የዓለም ዋንጫው የዕጣ ድልድል ቋት ውስጥ የገቡ ሃገራት ይፋ ሆኑ

​​​

ፔሩ ለ2018 የሩሲያው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የመጨረሻዋ 32ኛ ተሳታፊ ሃገር መሆኗን ካረጋገጠች በኋላ ፊፋ አርብ ህዳር 22፣ 2010 ዓ.ም በይፋ ለሚወጣው የመጨረሻው አራት የምድብ ድልድል የዕጣ አወጣጥ ቋት ውስጥ የገቡ ሃገራትን አሳውቋል።

የዓለም አቀፉ የእግርኳስ አመራር አካል በመስከረም ወር ስፖርታዊ መርሆዎችን መሰረት በማድረግ  እያንዳንዱ ስምንት ሃገራትን ያካተተ አራት የዕጣ ማውጪያ ቋቶች እንደሚኖሩ ገልፃ ነበር። 

ፊፋ በአራቱ ቋቶቹ ውስት የሚገቡ ሃገራትን ለመለየትም በፊፋ/ኮካ ኮላ የዓለም ሃገራት ደረጃን እንደሚጠቀምም መግለፁ ይታወሳል። 

በዚሁ መሰረት አዘጋጇን ሃገር ሩሲያን በመጀመሪያው ቋት ውስጥ ቀዳሚ በማድረግ እና በአንድ ቋት ውስጥ የሚገኙ ሃገራት በአንድ ምድብ ውስጥ ገብተው እርስ በእርስ እንዳይገናኙ ሆነው አራቱ ቋቶች ውስጥ የተካተቱን ሃገራት ዝርዝርን እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል። 

ቋት 1 ቋት 2 ቋት 3 ቋት 4
 ሩሲያ  ስፔን ዴንማርክ ሰርቢያ
 ጀርመን ፔሩ  አይስላንድ ናይጄሪያ
ብራዚል ስዊዘርላንድ ኮስታ ሪካ አውስትራሊያ
ፖርቱጋል እንግሊዝ ስዊዲን ጃፓን
አርጄንቲና ኮሎምቢያ ቱኒዚያ ሞሮኮ
ቤልጂየም ሜክሲኮ ግብፅ ፓናማ
ፖላንድ ኡራጓይ ሴኔጋል ደ ሪፐብሊክ
ፈረንሳይ ክሮሺያ ኢራን ሳ. አረቢያ

የመጨረሻው የድልድል የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት አርብ ህዳር 22፣ 2010 ዓ.ም በሞስኮ የክሪምሊን ቤተመንግስት እንደሚወጣ ፊፋ በመግለጫው አሳውቋል። 

Advertisements