ግጭት / ሮናልዶ እና ራሞስ መካከል ቁርሾ ተፈጥሯል

 

የሁለቱ ኮከቦች ፍጥጫ ማየሉን ከወደ ስፔን የሚሰሙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የምንግዜም የሪያል ማድሪድ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ክርስትያኖ ሮናልዶ እና ሰርጂዮ ራሞስ መሃል ንፋስ ከገባ መሰንበቱ የተሰማ ሲሆን ሁለቱም ኮከቦች በመልበሻ ክፍልም ጭምር ግጭታቸው አደባባይ መውጣት ጀመረ እንደቆየም እየተነገረ ይገኛል፡፡

እንደ ማርካ ዘገባ ከሆነም ካሳለፍነው ክረምት ጀምሮ ክርስትያኖ ሮናልዶ የመልበሻ ክፍል የበላይቱን ያጣ ሲሆን በሪያል ማድሪድ ቤትም ሰርጂዮ ራሞስ የመልበሻ ክፍሉን መምራቱን መቀጠሉን የዜና አውታሩ ዘግቧል፡፡ በተለይም ፖርቱጊዝ ተናጋሪዎቹ ፔፔ እና ፋብዮ ኮንትራኦ ሎስ ብላንኮዎቹን መልቀቃቸውን ተከትሎ እንዲሁም የክርስትያኖ ሮናልዶ የልብ ወዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ጀምስ ሮድሬጌዝ ወደ ባየር ሙኒክ በውሰት ውል ማቅናቱን ተከትሎ ክርስትያኖ ሮናልዶ በመልበሻ ክፍሉ ባየተዋር የሆነ ሲሆን

በአንጻሩ ደግሞ በማድሪድ ተስፈኛ ኮከቦች የሚከበረው ሰርጂዮ ራሞስ በናቾ በዳኒ ካርቫል በማርኮ አሴንሲዮ እና ኢስኮ ታግዞ የመልበሻ ክፍሉን መምራቱን መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡ በተለይም ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ስፔን ከሩሲያ ጋር አድርጋው በነበረው እና 3-3 አቻ  ከተለያየችበት  ጨዋታ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው አስተያየት የሁለቱ ተጨዋቾችን ቁርሾ ያረጋገጠ ሆኗል፡፡

ከጋዜጠኞች ክርስትያኖ ሮናልዶ ሪያል ማድሪድን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ይለቃል የሚል ጥያቄን የደረሰው ስፔናዊው የመሀል ተከላካይ  ˝የማውቀው ነገር የለም  ስለዚህ ጉዳይ ራሱን ሄዳቹ ጠይቁት በማለት የመለሰው አስደንጋጭ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

Advertisements