አርሰናል ከ ቶተንሃም | የጨዋታ ቅድመ ቅኝት

መቼ? ቅደሜ ህዳር 9፣ 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ09:30

የት
? ኤመራትስ ስታዲየም

በምን የቴሌቭዥን ጣቢያ
? ስካይ ስፖርት ፕሪሚየር ሊግ (በእንግሊዝ)፣ ሱፐርስፖርት (በአፍሪካ ከሰሃራ በታች)፣ ቢኢንስፖርት (በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ

ቁጥራዊ መረጃዎች

የሁለቱ ክለቦች የእርስ በእርስ ግንኘነት 

ባለፉት አምስት ግንኙነታቸው፡ አርሰናል ድል1፣ ቶተንሃም ድል1 አቻ3 

በፕሪሚየር ሊጉ ግንኙነታቸው፡ አርሰናል ድል80፣ ቶተንሃም ድል11፣ አቻ21

የእርስበእርስ ግንኙነት በአጠቃላይ ጨዋታዎች ላይ፣ አርሰናል ድል80፣ ቶተንሃም ድል 62፣ አቻ 51

  • አርሰናል ከቶተንሃም ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጋቸው ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ማሸነፍ አልቻለም። (ሁለት ጊዜ ሲሸነፍ፣ አራት ጊዜ ዳግሞ አቻ ተለያይቷል።)
  • አርሰናልና ቶተንሃም በዚህ የውድድር ዘመን እስካሁን ባደረጓቸው 11 ጨዋታዎች እያንዳንዳቸው 20 ግቦችን አስቆጥረዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ ቶተንሃም 16 ግቦች ከተቆጠሩበት አርሰናል ባነሰ ሰባት ግቦች ብቻ መረቡን ደፍረዋል።
  • አርሰናሎች በፕሪሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ በሜዳቸው ያደረጓቸውን 10 ጨዋታዎች በሙሉ ማሸነፍ ችለዋል። (አምስት በ2017/18 እና አምስት በ2016/17)
  • ካለፈው የውድድር ዘመን መጀመሪያ አንስቶ አርሰናል ከየትኛውም የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ በላቀ 12 ግቦች በፍፁም ቅጣት ምት ተቆጥሮበታል።
  • ፒተር ቼክ በአርሰናል ከተመቱበት 13 የፍፁም ቅጣት ምቶች አንዱን ማዳን አልቻለም።
  • ፓውሎ ጋዛኒጋ በፕሪሚየር ሊጉ የቶተንሃምን ግብ የጠበቀ 15ኛ ግብ ጠብቂ ሲሆን፣ ካደረጋቸው ጨዋታዎች ከኢያን ዎከር፣ ሂጎ ሎሪስ እና ሚሸል ቮርም ቀጥሎ ዝቅተኛ ግቦች የተቆጠሩበት ግብጠባቂ ነው።
  • በዚህ የውድድር ዘመን ከተቆጠሩ የቶተንሃም ግቦች ለ40 በመቶው መቆጠር የሃሪ ኬን እጅ አለበት።
  • ከወቅተ የፕሪሚየር ሊጎ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች እያንዳንዱ ክለቦች ላስቆጠራቸው ግቦች ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግም ኬን ቀዳሚው ነው። 
  • በአማካኝ የኳስ ቁጥጥር ሁለቱ ክለቦች አይለያዩም። የሁለቱም አማካኝ የኳስ ቁጥጥር 58.4 ከመቶ ነው። ኳስን በሚገባ በመቀባበሉ ረገድ ግን አርሰናል በጣም በጥቂቱ ብልጫ አለው። (አርሰናል 84. ከመቶ፣ ቶተንሃም 83.9 ከመቶ)

የቡድን ዜናዎች

አርሰናል ከደርቢው ጨዋታ የመጨረሻው ሰዓት በፊት ከጥር ወር መጀመሪያ አንስቶ በጉዳት ላይ ለቆየው ለሽኮድራን ሙስታፊ እና በብሽሽት ጉዳት ምክኒያት ከወራት በላይ ከሜዳ ለራቀው ዳኒ ዌልቤክ ለዚህ ጫዋታ መድረስ አለመድረሳቸውን የአቋም መለኪያ ምርመራ በማድረግ እንደሚያረጋግጥ ይጠበቃል።

ሁለቱም ተጫዋቾች ስፐርስን የሚገጥመው ቡድን ውስጥ እንደሚካተቱ ሲጠበቅ፣ በአንፃሩ ኦሊቪየ ዥሩ በፈረሳይ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ላይ የታፋ ጉዳት የገጠመው በመሆኑ ከዙህ ጨዋታ ውጪ ሲሆን የረጅም ጊዜ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ላይ የሚገኘው ሳንቲ ካዛሮላም አሁንም በዚህ ጨዋታ ላይ የማይኖር ተጫዋች ነው።

በሌላ በኩል እስካሁን የጤናቸው ጉዳይ እርግጥ ካልሆኑት በርካታ የቶተንሃም ተጫዋቾች መካከል ሃሪ ኬን አንዱ ነው። ኬን (በጉልበት) ጉዳት፣ ዴሌ አሊ (በቋንጃ)፣ ዊንክስ (በቁርጭምጭሚት)፣ ሎሪስ (በብሽሽት)፣ እና ቮርም (በጉልበት) በደርቢው ጨዋታ ላይ የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው። የቶቢ አልደርዊልድ፣ ቪክቶር ዊንያማ እና ኤሪክ ላሜላ ጉዳት ግን ተጫዋቾቹ በዚህ ጨዋታ ላይ እንዳይሰለፉም የሚያስገድዳቸው ነው። 

Advertisements