ኤሪክ ካንቶና የኔይማር ወደ ፒ ኤስ ጂ ያቀናበትን ዝውውር ተቸ

20.jpg

የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ የነበረው ኤሪክ ካንቶና ኔይማር ትላልቅ ኮከብ ተጫዋቾች ካሉበት ባርሴሎናን ለቆ ወደ ብዙም ትኩረት ወደ የማይሰጠው የፈረንሳዩ ሊግ ኣ ማቅናቱ እንዳስገረመው በመናገር ዝውውሩን ተችቷል፡፡

ብራዚላዊው ኮከብ በክረምቱ የዝውውር መስኮት 198 ሚሊየን ፓውንድ ወጥቶበት በአለም የዝውውር ሪከርድ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ማቅናቱ ይታወሳል፡፡ተጫዋቹ ባርሴሎናን ከሚያክል ቡድን ለቆ ቡዙም ጠንካራ ፌክክር ወደ የማይደረግበት የፈረንሳይ ሊግ ኣ ማምራቱ እስካሁንም ለአንዳንድ እግርኳስ ተንታኞች እና የቀድሞ ተጫዋቾች አግራሞትን መፍጠሩ ቀጥሏል፡፡

የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው ኤሪክ ካንቶናም በተጫዋቹ ዝውውር ዙሪያ ላይ አስተያየቱን ከሰጡት ውስጥ ተካቷል፡፡ነገርግን ወደ ፈረንሳይ ለምን እንዳቀና ይጠይቃል፡፡

19

“በ 25 አመትህ ለብራዚል እና ለባርሴሎና መጫወት የምትችል ከሆነ ወደ ፈረንሳይ ሄደህ ከ ጎንጎ እና አሚንስ ከሚባሉ ቡድኖች ጋር ለመጫወት ወደ እዛ ለመሄድ ስትወስን እራስህን መጠየቅ አለብህ፡፡ቻምፒየንስ ሊግ? ቻምፒየንስ ሊግ እራሱ በአመት የምትጫወተው 10 ጨዋታዎችን ነው፡፡ኔይማር ወደ ፈረንሳይ ለምን እንደመጣ ሊገባኝ አልቻለም፡፡”

ለፈረንሳዮቹ ኦግዜር እና ማርሴ መጫወት የቻለው ካንቶና አያይዞ የፈረንሳይ ሊግ ኣ መመልከት ፍላጎቱ እንዳልሆነ እና ደረጃው ዝቅ ያለ መሆኑን አስረድቷል፡፡“የፈረንሳይ የክለቦች ጨዋታን አልመለከትም፡፡ምን የሚያሳየኝ ነገር አለ? ፒ ኤስ ጂ ከ ጎንጎ ሲጫወት ለማየት? ያ ለኔ የሚመስጥ ጨዋታ አይደለም፡፡

ሀቭየር ፓስቶሬ እስካሁን ለፒ ኤስ ጂ ይጫወታል? ፓስቶሬን እወደዋለው፡፡ብዙ ጊዜ አይጫወትም? እሄ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ምናልባት የማልመለከተው ለዛ ሊሆን ይችላል፡፡እሺ ሀቲም ቤናርፋስ? ይጫወታል? አይጫወትም? በርግጠኝነት ሌሎቹን አልመለከታቸውም፡፡”ሲል ተናግሯል፡፡

ካንቶና በዚህ ወር ውስጥ በጉልህ ስሙ ሲነሳ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው በፓትሪክ ኤቭራ የስነምግባር ጉድለት ምክንያት የካንቶና 1995 ላይ ሴልሁርስት ፖርክ ላይ ማቲው ሲሞንስ የተባለውን የፓላስ ደጋፊን በኩንጉፉ የተማታበት ሁኔታ ሲታወስ አሁን ደግሞ በኔይማር ዝውውር ላይ በሰጠው አስተያየት ለሁለተኛ ጊዜ ስሙ ሊታወስ ችሏል፡፡

17.jpg

ኔይማር ወደ ፒ ኤስ ጂ ካቀና በኋላ ምንም እንኳን በቁጥር ደረጃ 11 ጎሎችን ማስቆጠር በመቻል ጠንካራ አጀማመር እያደረገ ቢሆንም ከቡድን ጓደኞቹ እንዲሁም ከአሰልጣኙ ኡናይ ኤምሬ ጋር በጥሩ መንፈስ እየሰራ አይመስልም፡፡በሊጉ መጀመሪያ አካባቢ ከኤዲሰን ካቫኒ ጋር የፍጹም ቅጣት ምት ለመምታት ሜዳ ላይ ሲነታረኩ የሚያሳዩ ምስሎች ወጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም ምክንያት ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር መያያዝ የጀመረ ሲሆን የሀገሩ ልጅ የሆነው ካስሚሮም ኔይማር ወደ ማድሪድ ቢመጣ የዋና ከተማው ቡድን እጁን ዘርግቶ እንደሚቀበለው ተናግሯል፡፡“እሱ ኮከብ ተጫዋች ነው፡፡ምን ማድረግ እንደሚገባው ያውቃል፡፡ትልቅ ተጫዋች ስለሆነ ሁልጊዜ ሪያል ማድሪድ በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቀዋል፡፡በርግጥ ወደእኛ እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለው፡፡ ነገርግን በአሁን ጊዜ በፈረንሳይ ደስተኛ ነው፡፡ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡

 

Advertisements