ራኒያሪ የጣሊያን አሰልጣኝ ስለመሆን እንደሚያጤኑበት ገለፁ

የናንተሱ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒየሪ የአራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮኗ ጣሊያን ለሩሲያው ዓለም ዋንጫ ማለፍ በመቻሏ ከባድ የሃዘን ስሜት ውስጥ የምትገኝ መሆኗን ተከትሎ የጣሊያን አሰልጣኝ ስለመሆን እንደሚያጤኑበት ተናግረዋል።

ጣሊያን ከ1958 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ማድረግ ሳትችል ስትቀር የቡድኑ አሰልጣኝ የነበሩትን ጂያን ፒየሮ ቬንቱራን ካሰናበተች በኋላ አዲስ አሰልጣኝ እያፈላለገች ትገኛለች።

ጣሊያን በደርሶ መልስ ድምር ውጤት በስዊዲን 1ለ0 ከተሸነገች በኋላ ካርሎ አንቸሎቲ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ እንደሚሆን የተገመተ ቢሆንም፣ ሌላው ጣሊያናዊ እና የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ መሆን የቻሉት ራኒየሪ ለሃገሪቱ ጥሪ ምለሽ ለመስጠት ፈቃፈኛ ሆነዋል።

“የጣሊያን አሰልጣኝ እሆናለሁ? አስብበታለሁ። ነገር ግን ያ በእኔ [ፍላጎት] ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም። ከናንተስ ጋር ኮንትራት ያለኝ። በመሆኑም ከፕሬዝዳንቱ ጋር መነጋገር ይኖርብኛል።” ሲሉ የ66 ዓመቱ አሰልጣኝ ለስካይ ስፖርት ኢታልያ ተናግረዋል።

“እንደማክሲ አሌግሪ፣ አንቶኒዮ ኮንቴ፣ እና ካርሎ አንቸሎቲ ያሉ ስሞችን አንብቤያለሁ። በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው እላለሁ። በዚያ ዝርዝር ላይ ያሉት በሙሉ እጅግ በጣም ጥሩ ናቸው።

“በጣሊያን የአሰልጣኝ ሁኔታ ሁለተኛ ነገር ነው። ምክኒያቱም በቶሎ ስሜታችን ይነካል። ስለዚህ ነገሮች መለወጥ ይኖርባቸዋል። በርካታ ጥሩ ወጣት ተጫዋቾች አሉ። ስለዚህ ተመልሰን በሁለት እግራችን መቆም ይኖርብናል።

“ጣሊያን ለ60 ዓመታት የዓለም ዋንጫው አምልጧት አያውቅም። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በሁለቱም እግርህ መልሰህ እስክትቆም ድረስ ስሜታህ ሊነካ ይገባል።”

የራኒየሪው ናንተስ ቅዳሜ በፈረንሳዩ ግዙፍ ክለብ ፒኤስጂ 4ለ1 በሆነ ውጤት ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ በሊግ 1 በአምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

Advertisements