ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለሴካፋ ዋንጫ 23 ተጫዋቾችን ጥሪ ተደረገላቸው

ዋልያው በኬንያ አስተናጋጅነት ከህዳር 24 እስከ ታህሳሰ ዘጠኝ በሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ ላይ ላይ የሚሳተፉ 18 ተጫዋቹን ይፋ አድርጓል፡፡ የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዳይቋረጥ በሚል ከክለቦች ሁለት ተጫዋቾች ብቻ የተመረጡ ሲሆን  በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ዋልያዎቹ ለዚህ ውድድር አዳዲስ እና ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ጥሪ አስተላለፍዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ተስፋዮ አለባቸው እና መስዑድ መሀመድ ልምድ ካላቸው ውስጥ ሲካቱቱ ተስፈኞቹ የደደቢቱ አጥቂ አቤል ያለው እና የመቀሌ ከተማው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ለብሄራዊ ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሪ ተላልፎላቸዋል፡፡  ብሄራዊ ቡድኑ ህዳር ከነገ በስተያ ህዳር 13 ልምምዱን በአዲስ አበባ ስቴዲየም ለመጀመር ማቀዱ የተሰማ  ሲሆን ከነገ ጀምሮም ጥሪ የተላለፈላቸው ተጫዋቾች ወደ ካፒታል ሆቴል በመሄድ ሪፖርት እንዲያደርጉ ትህዛዝ እንደተሰጣቸውም ተሰምቷል፡፡

ለብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ የተላለፈላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው።

ግብ ጠባቂዎች

 • ታሪክ ጌትነት (ደደቢት)
 • ተ/ማርያም ሻንቆ (ሃዋሳ)
 • በረከት አማረ (ወልዋሎከተማ)

ተከላካዮች

 • ቴድሮስ በቀለ (መከላከያ)
 • አበበ ጥላሁን (ሲዳማ ቡና)
 • አበባው ቡጣቆ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
 • አናጋው ባደግ (ድሬዳዋ)
 • ግርማ በቀለ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
 • አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከተማ)
 • ተመስገን ባስትና (አርባምንጭ ከተማ)
 • ሄኖክ አዱኛ (ጅማ አባጅፋር)

አማካዮች

 • ሳምሶን ጥላሁን (ኢትዮጵያ ቡና)
 • ተስፋዮ አለባቸው (ወልዲያ ከተማ)
 • ከነዓን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)
 • እንዳለ ከበደ (አርባምንጭ ከተማ)
 • በሃይሉ ተሻገር (ኢትዮኤሌክትሪክ)
 • ብሩክ ቃሊቦሬ (ወልዲያ ከተማ)
 • መሱድ መሀመድ(ኢትዮጵያ ቡና)

አጥቂዎች

 • አቡበከር ሳኒ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
 • አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)
 • አብዱራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ)
 • አማኑኤል ገ/ሚካኤል (መቀሌ ከነማ)
 • አቤል ያለው (ደደቢት)

 

 

Advertisements