“ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ ሁሉንም ዋንጫዎች የማንሳት አቅም አለው”- ዝላታን ኢብራሂሞቪች

Jose Mourinho trusted Zlatan Ibrahimovic would make a full recovery

ከወራት የጉልበት ጉዳት በኋላ ባሳለፍነው ቅዳሜ ማንችስተር ዩናይትድ ኒውካስል ዩናይትድን 4-1 በረታበት የሊጉ ጨዋታ ላይ ተቀይሮ መግባት የቻለው ዝላታን ኢብራሂሞቪች ቀያዮቹ ሰይጣኖች በውድድር አመቱ ውጤታማ ጊዜን እንደሚያሳልፉ እና በሚወዳደሩባቸው በሁሉም የዋንጫ ውድድሮች ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ተናግሯል፡፡

የ36 አመቱ ስዊዲናዊ አጥቂ ባሳለፍነው አመት ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ በኢሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ከባድ የሚባል የጉልበት ጉዳት ካስተናገደ ከ7 ወራት በኋላ ወደ ሜዳ መመለሱን ተከትሎ ከስካይ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ ሁላችንም እዚህ ነን ድል ማድረግ እንፈልጋለን ቅድምያ የምንሰጠው ለማሸነፍ ነው፡፡

ፖግባን ተመልከቱ ትልቁ አቅም እና ብቃት ያለው ተጫዋች ነው ፡፡ ከጉዳቱ ከተመለሰ በኋላም በሳምንቱ መጨረሻም ይህንን ከእርሱ አይተናል ፡፡ አሰልጣኛችንም በዚህ ሰሞን ደስተኛ ነው::  ምክንያቱም ሁሉም ተጫዋቾቹ ከጉዳት ነጻ ሆነው የተሟላ ስብስብ ማግኘት የቻለው በዚህ ሳምንት ነው፡፡

አሁን ሳስበው ማንችስተር ዩናይትድ ሁሉንም ዋንጫዎች የማሸነፍ አቅም አለው ፡፡ ባሳለፍነው አመት ሁለት ዋንጫዎችን ከፍ ማድረግ ችለናል፡፡ በዚህ አመት ደግሞ ካለፈው ይበልጥ ተጠናክረናል፡፡ እመኑኝ ሁሉንም የማድረግ አቅም አለን ፡፡ በማለት ደጋፊዎች  በውድድር አመቱ ጠንካራውን ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚመለከቱ ተናግሯል፡፡  

አሁን ከጉዳቴ ሙሉ በሙሉ ማገገም ችያለው ለስድስት ወራት ከግማሽ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ብርቅም በፍጥነት ለማገገም ከባድ የተባሉ ልምምዶችን በቀን ውስጥ ለ5 እና ስድስት ሰዓታት ስሰራ ቆይቻለው ከጉዳቱ ለማገገም ምን ያህል እንዳጠረ ተናግሯል፡፡

ዝላታን ኢብራሂሞቪች ማንችስተር ዩናይትድ የፊታችን ረቡዕ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ወደ ስዊዘርላንድ አቅንቶ ባስልን በሚገጥምበት የምድቡ 5ኛ ጨዋታ ላይ ለቀያዮቹ ሰይጣኖች የመጀመሪያውን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

 

 

Advertisements