ቶኒ ፑሊስ ከዌስትብሮም አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ


ቶኒ ፑሊስ ከዌስት ብሮምዊች አልቢዮን ዋና አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸውን ክለቡ ገልፅዋል።

የ59 ዓመቱ ሰው ባደርጓቸው ያለፉት 21 የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ማሸነፋቸው እንዲሁም ቅዳሜ በቼልሲ የ4ለ0 ሽንፈት የደረሰባቸው መሆኑ ሃውትሮንስን እዲሰናበቱ ምክኒያት ሆኗል።

ዌስት ብሮም በአሁኑ ጊዜ ካዳረጋቸው የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ 12 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለት ጨዋታዎችን  በማሸነፍና ዘጠኝ ግቦችን ብቻ ከመረብ ላይ በማሳረፍ ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ደረጃ ብቻ ከፍ ብሎ ይገኛል።
የክለቡ ኃላፊ የዌልሳዊን አሰልጣኝ ስንብት አስመልክተው “ይህ ውሳኔ በቀላሉ የተወሰደ አይደለም። ሁልጊዜም የክለቡ ፍላጎት [ቀዳሚ] በመሆኑ እንጂ። 

“በውጤትች ላይ የተመሰረተ ቢዝነስ ላይ እንገኛለን። ውጤታችን ደግሞ ካለፈው የውድድር ዘመን መጠናቀቂያ ጊዜ አንስቶ እስከዚህ የውድድር ዘመን ድረስ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር። 

“ቶኒ የባለቤት ለውጥን ጭምር ባካተተው በክልቡ የሽሽግሩ ወቅት ላበረከተው አስተዋፅኦ እና ጠንካራ ስራ አድናቆታችንን እናቀርባለን። መጪው ጊዜ መልካም እንዲሆንለትም እንመኛለን።” ሲሉ ገልፀዋል።

በቋሚነት የክለቡን ቀጣይ አሰልጣኝ ፈልገው እስኪያገኙ ድረስ የክለቡን ምክትል አሰልጣኝ ጋሪ ሜግሰንን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት መሾሙንም ክለቡ ገልፅዋል።

Advertisements