የዌስት ሃም ደጋፊዎች ወደፖሊስ የአደጋ ጊዜ ስልክ እንዳይደውሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

የዌስት ሃም ደጋፊዎች በቡድናቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለማሰማት የፖሊስ የአደጋ ጊዜ የስልክ ቁጥር ወደሆነው 999 መደወላቸውን እንዲያቆሙ ከፖሊስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ዴቪድ ሞስይስ በክለቡ አሰልጣኝነታቸው የመጀመሪያቸው በሆነ ጨዋታ መዶሻዎቹ እሁድ በዊል ሂዩስ እና ሪቻርሊሰን ግቦች በቪካሬጅ ሮድ ስታዲየም በዋትፎርድ 2ለ0 በሆነ ውጤት ሽንፈት ገጥሟቸዋል።

ይህ ደግሞ አንዳንድ ደጋፊዎች ያለባቸውን ቅሬታ ከመጠን ባለፈ እንዲያንፀባርቁ ምክኒያት የሆነ ይመስላል የለንደኑ ኤክሴክስ ፖሊስ ኃይል ቁጥጥር ክፍል ደጋፊዎቹ የአደጋ ጊዜውን መጠቀማቸውን እንዲያቆሙ ማስጠንቀቂያ እንዲያስተላልፍ አድርጎታል።

የፖሊስ ኃይሉ በይፋዊ ትዊተር ገፁ ላይ “አሁንም በድጋሚ ዌስትሃም ዩናይትድ ዛሬ ሽንፈት የደረሰበት በመሆኑ ወደ999 መደወሉ ቀጥሏል። እናም ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እርገጠኛ የሆናችሁበትን ነገር ማድረጋችሁ ተቀባይነት የሌለውን ነገር ነው! ድርጊቱ ፈፅሞ ጊዜ የሚያቃጥል ተግባር ነው። #999 የአደጋ ጊዜ ብቻ ነው።” ሲል ማሳሰቢያ አዘል መልዕክቱን አስተላልፏል።

በሁለቱ ክለቦች የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ በወቅታዊው የፕሪሚየር ሊግ ደረጀ በ18ኛ ላይ በሚገኙት የዌስትሃም ደጋፊዎች የተመልካች መቀመጫ በኩል “ቦርዱን አሰናብቱት” የሚል የተቃውሞ ድምፅ ሲሰማም ነበር ተሰምቷል።

ዌስት ሃም  ሞየስን ከቀጠረ በኋላ የፊታችን አርብ በፕሪሚየር ሊጉ በሜዳው ለመጀመሪያ ጊዜ ሌስተር ሲቲን ይገጥማል።

Advertisements