ሮናልዲንሆ የፔፕ ጓርድዮላን የማንችስተር ሲቲ ስኬት ከወዲሁ ገምቷል

Pep Guardiola's Man City are enjoying a fantastic start to the season

የቀድሞ የባርሴሎና ኮከብ ሮናልዲንሆ ፔፕ ጋርዲዮላ ከፍራንክ ራይካርድ ስንብት በኋላ ኑካም ደርሶ ሮናልዲንሆን ቢሸኝም ብራዚላዊ የቀድሞ የአለማችን ምርጥ እግር ኳሰኞ ስፔናዊው አሰልጣኝ በማንችስተር ሲቲ ቤት መልካም አመታትን እንደሚያሳልፍ ግምቱን አስቀምጧል፡፡

ፔፕ ጓርዲዮላ በባርሴሎና ቤት የ4 አመታት ቆይታው 2 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና 3 የላሊጋ ዋንጫዎችን ጨምሮ በድምሩ  14 ዋንጫዎችን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን እንደ ሮናልዲንሆ እምነት ከሆነም ፔፕ ጋርድዮላ በባርሴሎና ቤት ያሳለፈውን ስኬታማ ጊዜያት በማንችስተር ሲቲ ቤትም ለመድገም አቅሙ እንዳለው  ለዴይሊ ሚረር ተናግሯል፡፡

“በእግር ኳስ ህይወቴ ከተመለከትኳቸው እና ካሰለጠኑኝ አሰልጣኞች መካካል ምርጥ አሰልጣኝ  የምለው ፍራንክ ራይካርድን ቢሆንም ፔፕ ጓርዲዮላ የሚያሰለጥናቸውን ቡድኖች የሚመራበት መንገድ አስገራሚ የሜዳ ላይ  ኳስ ቅብብላቸው  እና የሚያዝናና ኳስ ጨዋታቸው ሁሉም እግር ኳስ አፍቃሪ ሊወደው የሚችለው አይነት ነው፡፡”  በማለት ፔፕ ጋርዲዮላን አወድሷል

በማንችስተር ሲቲ ቤት በ17 ጨዋታዎች 10 ግቦችን ማስቆጠር ስለቻለው ስለ ሀገሩ ልጅ ብራዚላዊው ኮከብ ጋብሬል የሱስ ብቃት ሲጠየቅም እርሱ በቀጣይ የማንችስተር ሲቲ ተቀዳሚ የፊት መስመር አማራጭ እንደሚሆን አምናለው ፡፡ የሚጫወትበትን መንገድም እወድለታለው፡፡ እመኑኝ እርሱ በማንችስተር ሲቲ ቤት ልዩነት ፈጣሪ ተጫዋች መሆን ይችላል፡፡ በማለት የሀገሩ ልጅ በቀጣይ የሲቲ ኮከብ እንደሚሆን ግምቱን አስቀምጧል፡፡

 

Advertisements