ሰበር ዜና / የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ በአሜሪካ በሰራው ወንጀል ቅጣት ተጥሎበታል

Image result for Romelu Lukaku

ባሳለፍነው ክረምት ማንችስተር ዩናይትድን በ75 ሚሊየን ፓውንድ ከኤቨርተን የተቀላቀለው ሮሜሉ ሉካኩ ምንም እንኳ ባሳለፍነው ሳምንት ከጎል ድርቁ ተላቆ በሊጉ ግብ አስቆጥሮ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎችን ቢያስደስትም ከወደ ሎስ አንጀለስ የተሰማው ዜና ለሮሜሎ ሉካኩ ወዳጆች እና የቀያዮቹ ሰይጣኖቹ ደጋፊዎች ግን አስደንጋጭ ሆኗል፡፡

የማንችስተር ዩናይትዱ ኮከብ ሮሜሉ ሉካኩ ከወራት በፊት ለእረፍት ወደ አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ባቀናበት ወቅት በፈጸመው  ወንጀል ምክንያት እስከ ስድስት ወራት  ሊደርስ የሚችል የእስር ቅጣት ሊያስተላልፈበትን የሚችለበትን ጥፋት መፈጸሙ ተሰምቷል፡፡

ቢቢሲ ዛሬ ምሽት በሰበር ዜና እንዳስነበበው ከሆነ የማንችስተር ዩናይትዱ ውዱ አጥቂ በወርሀ ሀምሌ ለእረፍት በአሜሪካ በሚገኝበት ሰዓት  ከባድ በሆነ የሙዚቃ ድምጽ የአካባቢውን ማሕበረሰብ መረበሹን ተከትሎ ከ5 አባወራዎች ቅሬታ በመቅረቡ  የቢቨርሊይ ፖሊስ ጣቢያ መኮንኖች ወደ ሉካኩ መኖሪያ ባቀኑበት ወቅት መኮንኖቹ ወደ ቤቱ ቢያቀኑም ምላሽ አለመስጠቱን ተከትሎ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተነግሯል፡፡

በአሜሪካ ህግ መሰረትም ከወንጀል ለማምለጥ ለፍትህ አካላት ምላሽ አለመስጠት ለስድስት ወራት ዘብጥያ የሚያስወርድ ቢሆንም   የሎስ አንጀለሱ ኤርፖርት ፍርድ ቤት ግን ሮሜሎ ሉካኩን  በ100 ዶላር ቅጣት ብቻ ያለፈው ሲሆን የከተማው ፖሊስ ለእርሱ ክስ ጉዳይ ያወጣውን 340 ዶላር ካሳ እንዲከፍልም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የሎስ አንጀለስ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ታህሳስ 18 ስለ በጉዳዩ ዙሪያ  የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ክስ ለማድመጥ ቀነ ቀጠሮ የያዘ ሲሆን ሆኖም በዚህ እለት ሮሜሎ ሉካኩ ይገኝ የሚል ትሕዛዝ ከፍርድ ቤቱ እንዳልመጣም ተሰምቷል፡፡

 

Advertisements