ሲቪያ ከ ሊቨርፑል | የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቅድመ ቅኝት

ዛሬ የሚገጥመውን ሲቪያን በምድብ ኢ በአንድ ነጥብ ቀድሞ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጠው የየርገን ክሎፑ ሊቨርፑል በዛሬ የማክሰኞ ምሽት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ወደጥሎማለፍ ዙሩ ማለፍ የሚችልበት ዕድል ይዞ ከስፔኑ ክለብ ሲቪያ ጋር ይፋለማል።

ጨዋታ ሲቪያ ከ ሊቨርፑል
ቀን ማክሰኞ፣ ህዳር 12
ሰዓት ምሽት 03:45

 የቀጥታ ስርጭት


Phil Coutinho

በዩናይትድ ኪንግደም ጨዋታው በቢቲ ስፖርት 2 ቻናል ላይ በቀጥታ ሲተላለፍ፣ ከሰሃራ በታች በአፍሪካ ሱፐር ስፖርት፣ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ቢኢን ስፖርት እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ከኢኤስፒኤን ስፖርት በተጨማሪ ፎክስ ሶከር ፕላስ ቴሌቪዥን እንዲሁም በኢንተርኔት ላይቭ ስትሪሚንግ ፎክስ ሶከር ማች ፓስ ይህን ጨዋታ በቀጥታ የሚያስተላልፉ የቴሌቭዥን ኩባንያዎች ናቸው።


የቡድኖቹ የተጫዋቾች ስብስብ


ቦታ የሲቪያ ተጫዋቾች
ግብጠባቂዎች ሪኮ፣ ሶሪያ፣ ፔሬዝ፣ ሶሪያኖ 
ተከላካዮች ኮርቺያ፣ ኪያር፣ ሌንግሌት፣ ካሪኮ፣ ኤስኩዴሮ፣ ፓሬሃ፣ ሜርካዳ፣ ካርሞና፣ አሞ
አማካኞች ክሮህን-ደህሊ፣ ሞንቶያ፣ ባኔጋ፣ ኮሬያ፤ ጊስ፣ ፒዛሮ፣ ንዞንዚ፣ ናቫስ፣ ሳራቢያ፣ ጋንሶ፣ ቫስኬዝ፣ ላሶ፣ ኩሮ፣ ፖዞ፣ ብሪሴ 
አጥቂዎች ቤን-ዬደር፣ ሙሬል፣ ኖሊቶ፣ ፈርናንዴዝ 

ሲቪያ እንግዳውን ቡድን ሊቨርፑልን ሲገጥም በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተከላካዮች ማሰለፉ አጠራጣሬ ነው። ዳኒኤል ካሪኮ እና ኒኮላስ ፔሬሃ በጉዳት ላይ ሲገኙ፣ ሰባስቲያን ኮርቺያ ደግሞ ቡድኑ ቅዳሜ ሴልታ ቪጎን ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ በገጠመው ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው።

እንደ ዊሳም ቤን-የደር እና ኼሱስ ናቫስ ያሉ ተጫዋቾች ደግሞ በቅዳሜው ጨዋታ ባይሰለፉም በምሽቱ ጨዋታ ላይ ግን እንደሚሰለፉ ይጠበቃል።

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች: ሪኮ፣ ኢስኩዴሮ፣ ኪያር፣ ላንግሌት፣ ጊስ፣ ንዞንዚ፣ ፒዛሮ፣ ባኔጋ፣ ናቫስ፣ ቤንስ-ዬደር፣ ኮሬያ

ቦታ የሊቨርፑል ተጫዋቾች
ግብጠባቂዎች ካሪዩስ፣ ሚኞሌ፣ ዋርድ
ተከላካዮች ሎቭረን፣ ጎሜዝ፣ ክላቫን፣ ሞሬኖ፣ ሮበርትሰን፣ ማቲፕ፣ ፍላናጋን፣ ማስቴርሰን፣ አሌክሳንደር-አርኖልድ
አማካኞች ዋይናልደም፣ ሚልነር፣ ኮቲንሆ፣ ሄንደርሰን፣ ግሩጂች፣ ላላና፣ ኦክሴድ-ቻምበርሌን፣ ቻን፣ ኢጃሪያ 
አጥቂዎች ፊርሚኖ፣ ሳላህ፣ ስተሪጅ፣ ማኔ፣ ሶላንኬ 

ሊቨርፑል አሁንም ድረስ አዳም ላላናን እና ናትናኤል ክላይንን ሳይዝ ይህን ጨዋታ ሲያደግ፣ ቀላል የሚባል ጉዳት የነበረበት ዦል ማቲፕ ግን ለዚህ ጨዋታ ወደሜዳ ይመስለታል።

ቅዳሜ ሳውዛምፕተንን ባሸነፈው ቡድን ውስጥ ተካቶ ያልተጫዋተው ጆ ጎሜ በዚህ ጨዋታ ላይ ቡድኑን ተቀላቅሎ ሊጫወት የሚችል ሲሆን፣ ግብ ጠባቂው ሎሪስ ካሪዩስም ሲሞን ሚኞሌን ተክቶ እንደሚጫወት ይጠበቃል።

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች፡ ካሪዩስ፣ ሞሬኖ፣ ማቲፕ፣ ሎቭረን፣ ጎሜዝ፣ ዋይናልደም፣ ሄንደርሰን፣ ኮቲንሆ፣ ሳላህ፣ ማኔ፣ ፊርሚኖ 


  የጨዋታ ቅድመ እይታ


Jurgen Klopp Liverpool

ሊቨርፑል ባለፈው በመስከረም ወር ከሲቪያ ጋር 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ ካደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሎ በጥር ወር በቶተንሃም የ4ለ1 ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ ግን በተከታታይ አራት ጨዋታዎችን በማሸነፍ እና ጨዋታዎቹ ላይ በአማካኝ ሶስት ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ወደመልካም አቋም መመለስ ችሏል።

በአንፃሩ ከወራት በፊት በሜዳው ማሸነፍ ተቸግሮ የቆየው የኤዱዋርዶው ቤሪዞሱ ሲቪያ የየርገን ክሎፑም ቡድን በሜዳው በመርታት ሶ 16 ቡድኖች የሚፋለሙበትን የጥሎ ማለፍ ዙር ለመቀላቀል ሶስት ነጥቦችን የማግኘት ውጥን ይዞ ይህን ጨዋታ ያደርጋል።

Advertisements