ክሎፕ፡ ስለፊርሚኖ ምን ማለት እችላለሁ? እሱ የቡድኑ ሞተር ነው

የርገን ክሎፕ የሮቤርቶ ፊርሚኖን ብቃት አድንቀው የፊት ተጫዋቹ በሊቨርፑል ቡድን ውስጥ “ሞተር” እንደሆነ ገልፀዋል።

ዘጠኝ ቁጥሩ በፊት ቦታ ላይ ተጭኖ በመጫወት በተቃራኒ ቡድን ተከላካዮች ላይ ችግሮቹን በመፍጠርና ለቡድን አጋሮቹ ግብ የማስቆጠሪያ በር በመክፈት ቀዮቹ በተከታታይ አራት ጨዋታዎችን ድል ማድረግ እንዲችሉ ጉልህ ሚና መጫወት ችሏል።

ምንም እንኳ ፊርሚኖ በሊቨርፑል ተከታታይ አራት ድሎች ላይ ማስቆጠር የቻለው አንድ ግብ ብቻ ቢሆንም፣ ክሎፕ ግን ብራዚላዊው ተጫዋች ወደግብ ማስቆጠር ሚናው እንደሚመለስ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ለክለቡ ይፋዊ ድረገፅ የተናገሩት የቀዮቹ አለቃ “ምን ዓይነት ተጫዋች ነው! ምን ማለት እችላለሁ? ኳስ ሲነጠቅ መልሶ ለማግኘት ይፋለማል። ደግሞ በድጋሚ ሲነጠቅ አሁንም ለማስመለስ ይፋለማል።

“የቡድኑ ሞተር ይመስላል። በጨዋታው [ከሳውዛምፕተን ጋር በተደረገው] ላይ ግብ አላስቆጠረም ወይም ግብ በተቆጠረበት ወቅት በግራና በቀኝ በኩል ርቆ ይገኝ ነበር። ወደግብም ሞክሯል፤ ተመልሶበታል። ነገር ግን ፊል [ኮቲንሆ] አስቆጠረው። ሆኖም በጨዋታው ላይ ንቁ ተሳትፎ ነበረው።

“ደጋፊው የሚያሳየውን አድናቆት እወደዋለሁ። ለማየትም የሚያስደስት ነው። እሱም ያ ይገባዋል። ምክኒያቱም ጠንከራ ሰራተኛ ነው።

“ሁሉም ተንካራ ሰራተኞች ናቸው። ነገር ግን በአጥቂነት ሚናህ ሁልጊዜም ግብ ማስቆጠር እንዳለብህ ታስባለህ። እሱም መቶ በመቶ ያደርገዋል።” በማለት ተናግረዋል።

ክሎፕ አክለውም “በቡድን ተጫዋቾች ደስተኛ ነኝ። በድጋሚ [ዛሬ ምሽት] አቅማቸውን ማስመስከር ይኖርባቸዋል። ነገር ግን በድጋሚ ባሳየነው መሻሻል ደስተኛ ነኝ።

“በዚህ የውድድር ዘመን በተወሰነ መልኩ ቀዝቀዝ ብለናል። ነገር ግን ተመልሰን ወደብቃታችን መጥተናል። ያ ደግሞ ጥሩ ምልክት ነው። እውነተኛ ጥሩ ምልክት። ስለዚህ በዚሁ መቀጠል አለብን።

“አሁን ስለምንፈልገው ማንኛውም ነገር መናገር እንችላለን። እናም [በሲቪያ] በድጋሚ ብንሸነፍ ስለአዲስ ነገር መናገር ይኖርብናል። ሆኖም ሁኔታው ያው ተመሳሳይ ነው።

“ውጤቶች ያስፈልጉናል። ነገር ግን ማድረግ የምንችለው ብቸኛ ነገር የሚቻለንን ያህል ዝግጁ መሆን ነው። እኛ እንደዚያ ነን ስለዚህ ወደዚያ እናምራና ኳስ ተጫውተን ጨዋታውን እናሸንፍ።”

Advertisements