ዩዴኔዜ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

ማክሰኞ ማለዳ አሰልጣኙን ሊዉጂ ዴል ኔሮን ያስናበተው የጣሊያኑ ክለብ ዩዴኔዜ ማሲሞ ኦዳን አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ገልፅዋል።

ዩዲኔዜ እሁድ በሴሪ ኣው በካግሊያሪ 1ለ0 ተሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ ከወራጅ ቀጠናው በሶስት ነጥቦች ብቻ ከፍ ብሎ መቀመጡ ዶል ኔሪ ከአሰልጠኝነት ስራቸው እንዲሰናበቱ ምክኒያት ሆኗል። 

ክለቡ ብዙ ጊዜ ሳያጠፋም ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ከቀድሞው ክለባቸው ፔስካራ የተሰናበቱትን ኦዶን ቀጥሯል።

Advertisements