“ፖል ፖግባ ናፍቆኛል” ፓብሎ ዲያባላ

Dybala admits he misses former team-mate Paul Pogba

በጣሊያኑ ሀያል ክለብ ጁቬንቱስ በውድድር ዘመኑ አስደማሚ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ፓውሎ ዲያባላ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ፖል ፖግባ እንደናፈቀው ተናግሯል፡፡ በ2015 ከፓሌርሞ ጁቬንቱስን ተቀላቅሎ በ2 አመታት የክለቡ ቆይታው 42 የሴሪያ ግቦችን ማስቆጠር የቻለው አርጀንቲናዊው ጥበበኛ የማንችስተር ዩናይትዱ ኮከብ አሁንም ከህሊናው እንዳልጠፋ ይፋ አደርጓል፡፡

በአሮጊቷ ቤት ምንም እንኳ ለ1 አመት ሁለቱ ኮከቦች በጋራ ቢጫወቱም አርጀንቲናዊው ኮከብ ከፍራንስ ፉትቦል ጋር ባደረገው ሰፋ ያለ ቆይታ “ፖግባ ናፍቆኛል እርሱ ምርጡ የቡድን ጋደኛዮ ነበር፡፡ አስገራሚ የሆነ ራዕይ አለው በዛ ላይ በራስ መተማመኑ አስደናቂ ነበር፡፡ እርሱ አለም ላይ ካሉ ምርጥ እግር ኳሰኞች መካከል ለኔ አንዱ ነው፡፡” በማለት የቀድሞ የቡድን አጋሩን መናፈቁን ተናግሯል፡፡

“በጁቬንቱስ ረጅም ጊዜ እቆያለው ብዮ ቃል መግባት አልፈልግም ፡፡ ይህ አመትም የመጨረሻዮ ነው ብዮም አላወራም፡፡ በእግር ኳስ የሚፈጠረው አይታወቅም ፡፡ ሆኖም  በዚህ ክለብ ግን ሁሉንም ዋንጫዎች በዚህ አመት ማንሳት እፈልጋለው፡፡” በማለት በውድድር ዘመኑ በአሮጊቷ ቤት ስኬታማ አመትን ማሳለፍ እንደሚፈልግ ይፋ አድርጓል፡፡

ሁሌም ሮናልዲንሆን ሳደንቅ እኖራለው ሆኖም ሊዮኔል ሜሲ ማለት ለኔ ልክ እንደ ማራዶና ነው ፡፡ ከእርሱ ጋር በብሄራዊ ቡድን ደረጃ መጫወቴ ያስደስተኛል ፡፡አዲሱ ሜሲ መባሌም ጫና ውስጥ አይከተኝም ፡፡ ሲል ስለሚያደንቃቸው ክዋክብት እንዲሁም አዲሱ ሜሲ መባሉ እንደማያስፈራው አብራርቷል፡፡

ፓብሎ ዲያባላ በውድድር ዘመኑ ጠንካራ የሚባል ጊዜን ከክለቡ ጋር ማሳለፉን የቀጠለ ሲሆን በአዲሱ የውድድር አመት ጅማሮም በ18 ጨዋታዎች አድርጎ  14 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

 

Advertisements