​ስንብት / የፀረ አበረታች መድሃኒት ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት ጋሪ ዋድለር አረፉ


ፅሁፍ ዝግጅት : በወንድወሰን ጥበቡ

ሃገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የዓለም አትሌቲክስ ማህበራትን ያመሱት የአትሌቶችን ብቃት ከፍ የሚያደርጉ አበረታች ማድሃኒቶችን መጠቀም ከስፖርቱ ዓለም እንዲወገድ ጠንከር ያለ ድምፃቸውን በማሰማት የሚታወቁት ዶክተር ጋሪ ዋድለር በ78 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የዋድለር ባለቤት  የባለቤታቸው ህልፈት መንስኤ ተደራራቢ የሆነ የነርቭ መታወክ እንደሆነ ለኒውዮርክ ታየምስ ገልፀዋል። 

ዋድለር በ1990 በአሜሪካን ኮንግረስ ፊት ቆመው አበረታች መድሃኒቶች የኦሎምፒክ ፉክክር መንፈስን ምን ያህል እንደጎዱ እና የታላላቅ አትሌቶችን ጤና ላይ ምን ያህል እክል እንደፈጠሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። 

አሜሪካዊው ዶክተር መሰል አበረታች ንጥረ ነገሮች በስፖርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚያግደው የዓለም አቀፉን የፀረ አበረታች መዳኒቶች ኤጄንሲ ኮሚቴንም በኃላፊነት መርተዋል። 

ዋድለር በ1989 “መድሃኔቶችና አትሌቱ” የተሰኘ መፅሃፍ በጋራ በመሆን የፃፉ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴም ፕሬዝዳንት እጅም የክብር ሽልማት መቀበል ችለዋል።

“እሱ [ዋድለር] የአትሌቶችን ጤናና ደህንንነት ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ላይ ፋና ወጊ ነው። እናም ይህን ሰው አጥተነዋል።” ሲሉ የአማሪካ የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ትራቪስ ታይጋርት የዶክተሩን ህልፈት አስመልክተው ተናግረዋል።

Advertisements