ናይጄሪያዊ አጥቂ ያኩቡ እግርኳስ መጫወት አቆመ

የቀድሞው የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ በ35 ዓመት ዕድሜው እግርኳስ መጫወት አቁሟል።

እ.ኤ.አ.ከጥር 2003 እስከ ግንቦት 2012  ድረስ ባሉ አስርት አመታት ለሚጠጉ ጊዜያት አብዛኛውን ጊዜ በአበይት የእንግሊዝ ክለቦች ውስጥ የተጫወተው ያኩቡ በ293 የሊግ ጨዋታ ተሳትፎ 114 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። 

ተጫዋቹ የቻይናውን ክለብ ጉዋንግዙን ከመቀላቀሉ በፊት አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜውን በፖርትማውዝ፣ ሚድልስብሮ፣ ኤቨርተን፣ ሌስተር እና ብላክበርን ክለቦች ውስጥ ተጫውቶ አሳልፏል።

በ2015 ዳግም ወደእንግሊዝ ከተመለሰ በኋላም በሬዲንግ እና ኮንቨንትሪ ሲቲ ክለቦች ውስጥ ተጫውቷል።

ያኩቡ በ2016 የቱርኩን ክለብ ካይሴሪስፖርን ለቆ ባለፈው የውድድር ዘመን ከጥር ወር እስከ እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ከኮንቨንትሪ ጋር ኮንትራት ከመፈራረሙ በፊት ከናሽናል ሊግ ተሳታፊው ቦርሀም ዉድ ጋር ልምምዱን ሲሰራ ቆይቷል። 

አጥቂው ለሃገሩ በ57 ጨዋታዎች ላይ 21 ግቦችን ከማስቆጠሩም በላይ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ያስቆጠራቸው 96 ግቦች ከየትኛውም ናይጄሪያዊ ተጫዋች የሚብጡ ሲሆን፣ ከዲድየ ድሮግባ በአምስት ግቦች ብቻ አንሶ በእንግሊዝ እግርኳስ ላይ ጎልተው መውጣት ከቻሉ አፍሪካውያን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ተርታም መቀመጥ ችሏል።

Advertisements