“አልናገርም። ስናገር አትረዱኝም።” – ሮናልዶ

የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ንግግሮቼ በተዛባ መንገድ ተወስደዋል በሚል ወቀሳ ሚዲያውን ተችቶ ክለቡ በሻምፒዮንስ ሊጉ አፖል ኒኮሲያን 6ለ0 ካሸነፈ በኋላ የቀረበለትን የቃለመጠይቅ ጥያቄ ሳይቀበል ቀርቷል። 

ሮናልዶ በህዳር ወር ማጀመሪያ በቡድኑ የስብስብ ሁኔታ ከሪያሉ አምበል ራሞስ ጋር በይፋ አለመግባባት ውስጥ ገብቶ ቆይቷል።

ከማክሰኞ ምሽቱ ድል በኋላ ቆሞ ለጋዜጠኞች ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረው ሮናልዶ “አልናገርም። ስናገር አትረዱኝም። 

“ከዚያም እናንተ [ሚዲያው] የላልኩትን ሌላ ነገር ትናገራላችሁ።” በማለት በስፍራው ለተሰበሰቡት ጋዜጠኞች ተጨማሪ ምላሽ ሳይሰጥ ባሉባት ትቷቸው ሄዷል።

ሮናልዶ በአፖል ላይ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሌሎች ሁለት ግቦችን ካሪም ቤንዜማ፣ እንዲሁም ተጨማሪ አንዳንድ ግቦችን ደግሞ ሉካ ሞድሪችና ሞድሪካንድ ናቾ ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል።

ውጤቱም ሪያልን በሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ ከምድቡ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አስችሎታል።

Advertisements