ቫልቬርዴ፣ መሲን በተቀያሪ ወንበር ላይ ያስቀማጡበትን ምክኒያት ገለፁ

የባርሴሎናው አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ አርጄንቲናዊውን ኮከብ፣ ሊዮኔል መሲን በተቀያሪ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ የመረጡበትን ምክኒያት ገልፀዋል።

የካታላኑ ክለብ በአሌያንዝ ስታዲየም ከጁቬንቱስ ጋር 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ከተለያየ በኋላ የቀድሞው የአትሌቲክ ክለብ አሰልጣኝ ባደረጉት ንግግር አርጄንቲናዊውን ተጫዋች በተቀያሪ ወንበር ላይ የማስቀመጥ ውሳኔ ላይ የደረሱት በሌላ የተለየ ምክኒያት ሳይሆን አስቀድመው እሱን ለማሳረፍ አስበውበት ስለነበር እንደሆነ ገልፀዋል። 

አሰልጣኙ አክለውም የ30 ዓመቱ ኮከብ ጉዳት እንዳልነረበት ለደጋፊው ማረጋገጫ ሰጥተዋል። 

“መሲ? እሱ ደህና ነው። በቅርብ ጊዜያት ብዙ ተጫውቷል። እሱን ለማሳረፍ ወይም በሁለተኛው አጋማሽ ልናስገባው ያሰብንበት ጊዜ የነበር መሆኑ እውነት ነው። 

“ጨዋታው በጣም የተጨናነቀ ሆኖ እንደሚጀምርና ማስከፈት እንደሚጠበቅንም ጠብቀን ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ውሳኔ ላይ ደረሰን። አሰልጣኞች በእንዳንድ ነገሮች ላይ በውስጣቸው ውሳኔ ላይ የሚደርስባቸው ጊዜያት እንዲህ ያሉ ናቸው።”

ባርሳ ለሁለት ጊዜያት ያህል ግብ ለማስቆጠር ሲቃረብ ምናልባት መሲ በጨዋታው ላይ ቢኖር ኖሮ ልዩነት ሊፈጥር ይችል ነበር። ተጫዋቹ በዚህ የውድድር ዘመን ከወዲሁ በላ ሊጋው ጨዋታዎች ላይ በዚህ ጥምር ሚናም ነበረው።

ቫርቬልዴ በእንፃራዊነት ቀዝቃዛ ለነበረው ጨዋታም ምላሻቸው አዎንታዊ ነበር።

“ወደዚህ የመጣነው ለማሸነፍና ሶስት ነጥቦችን ለመውሰድን አቅደን ነበር።” ሲሉም አቻ ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ ተናግረዋል።

“[በማሽነፍ] ባህሪ ነበር የተጫወትነው። ምክኒያቱም እነሱ አብዝተው የሚጫኑህ ቡድን ናቸው። ክፍተት ሲያገኙ ጉዳት ሊያደርሱብህ ይችላሉ። ምክኒያቱም ብቃቱ አላቸው። ነገር ግን ፍፃሜ ላይ ካለመድረስ በስተቀር እኛ ብልጫ የወሰድንባቸው በርካታ ጊዜያት ነበሩ። 

“ጨዋታውን ተቆጣጥረነዋል። የምድባችን አናት ላይ በመቀመጣችንም ደስተኛ ነን። የምንፋልገውም ይህንኑ ነበር።” ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።

Advertisements