ኤሲ ሚለን ችግር ውስጥ ነው

የበርካታ ምንጮች መረጃ እንደሚያማለክተው ከሆነ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ኤሲ ሚላን ሚዛናዊ የፋይናንስ ስርዓት ደንብን ጥሷል በሚል የቅጣት ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት ክለቡ ስለሚገኝበት የፋይናንስ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጠው ለክለቡ ጥያቄ አቅርቧል።

ክለቡ ባለፈው ክረምት ለቻይና የኢንቨስትመንት ግሩፕ ከተሸጠ በኋላ ባወጠው “ከፍተኛ” ወጪ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጥርጣሬ የገባው በመሆኑ ምክኒያት ክለቡ በቀጣይ የውድድር ዘመን ከአውሮፓ ውድድሮች ውጪ የመሆን ከባድ አደጋ ከፊቱ ተጋርጦበታል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ ሚላን ለተጫዋቾች ዝውውር ከ200 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ወጪ አድርጓል። እናም ከሁለት ሳምንት በፊት የሚለን ተወካዮች ስለወቅታዊው የክለቡ ቢዝነስ ዕቅድ ማብራሪያ እንዲሰጡ ወደአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዋናመስሪያ ቤት ማምራታቸውም ተዘግቧል።

ነገር ግን ክለቡን ገና ባለፈው የካቲት ወር በባለቤትነት የያዙት ቻይናዊው ሊ ዮንግሆንግ ከወዲሁ ክለቡን ኪሳራ ውስጥ የሚከተውን የዕዳ ጫና የሚጋራቸው ባለሀብት እያፈላለጉ መሆኑ በኤሲሚላን ባለሃብቶች ዙሪያ አጠራጣሪ ነገሮች እየታዩ ነው።

ኤሲ ሚላን በቻይናዊው ባለሃብት ዮንግሆንግ ቁጥጥር ስር ያለውና መሰረቱን ሉግዘምበርግ ያደረገው ሮሶኔሪ ስፖርት ኢንቨስትመንት ለክስ ኩባንያ የ99 በመቶ የድርሻ ባለቤትነት የተያዘ ነው። ባለሃብቱ ከለቡን ከቀድሞው የክለቡ ባለቤት ሲልቪዮ በርሉስኮኒ ለመግዛት 740 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ የስምምነት ወጪ አድርገውበታል። ግዢውን ለመፈፀመም ከፍተኛ የሆነ ወለድ ያለው ዕዳ ውስጥ ገብተዋል።

እንደፎርብስ መረጃ ከሆነም በለሃብቱ ተጨማሪ ዕዳ ውስጥ መግባቱን ስለማይፈልጉት ክለቡ ዳግም በቅናሽ ዋጋ ሊሸጥ ይችላል። ይህ ደግሞ ክለቡ ባለፉት አምስት ዓመታት ከገባበት የውጤት አዘቅት ለመውጣት ዋነኛ ተግዳሮት ይሆንበታል። 

Advertisements