ኮሎኝ ከ አርሰናል | የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ቅድመ ቅኝት

የጀርመኑ ክለብ ኮሎኝ በዛሬው በዩሮፓ ሊግ የምድብ ኤች ጨዋታ በቡንደስሊጋው ላይ እያሳየ የሚገኘውን መጥፎ ውጤት ወደጎን በማለት አርሰናልን ምሽት ሶስት ሰዓት በሜዳው ያስተናግዳል።

የቡድን ዜናዎች

ቤሊ ፍየሎቹ ባለፈው ቅዳሜ በቡንደስሊጋ በሜንዝ 1ለ0 ከመሸነፋውም በላይ በዚህ የውድድር ዘመን በ10 የሊግ ጨዋታቸው አንድ ጨዋታ ድል ማድረግ ሳይችሉ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ለመቀመጥ ተገድዋል። ይሁን እንጂ ባለፈው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታቸው ባቴ ቦሪሶቭን 5ለ2 ያሸነፉበትን ሰፊ ውጤት በልባቸው ይዘው እሁድ በለንደን ደርቢ ቀንደኛ ተቀናቃኛቸውን ቶተንሃምን 2ለ0 በሆነ ውጤት ያሸነፉትን እና በጥሩ የማሸነፍ  መንፈስ ላይ የሚገኙትን መድፈኞቹን በምሽቱ ጨዋታ በመርታት ወደቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የመሸጋገር ተስፋቸውን ለማለምለም ወጥነው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል በቶተንሃም ላይ ድል በመቀዳጀት በፕሪሚየር ሊጉ በስድስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አርሰናሎችም ከጀርመኑን ተጋጣሚያቸው ጋር በአቻ ውጤት መለያየት ብቻ በቀጣዩ 32 ክለቦች የሚሳተፉበት የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ዙር ላይ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የቀዳሚነት ትኬት እንዲቆርጡ ያስችላቸዋል።

የክለቦቹ ወቅታዊ የምድብ ደረጃ

ምድብ ኤች

# ክለብ ነጥብ
1 10
2 5
3 4
4 3


ግምታዊ አሰላለፎች

ኮሎኝ: ሆርን፣ ክለንተር፣ ማሮህ፣ ሶሬንሰን፣ ሩሽ፣ ዮጂች፣ ለህማን (አምበል)፣ ክሌመንስ፣ ቢተንኮርት፣ ኮርዶባ፣ ጊዩራሲ

የማይሰለፉ፡ ሄክቶር (በጉልበት ጉዳት)

አሰልጣኝ፡ ፒተር ስቶገር

አርሰናል: ኦስፒና፣ ኤልኒኒ፣ ደቡቺ፣ ሜርትሳከር፣ ሆልዲንግ፣ ኔልሰን፣ ፣ ዊሎክ፣ ዊልሼር፣ ማይትላንድ-ኒለስ፣ ዋልኮት (አምበል)፣ ዌልቤክ

የማይሰለፉ፡ ካዛሮላ (በእግር ጉዳት)፣ ዥሩ (በብሽሽት ጉዳት)

አሰልጣኝ፡  አርሰን ቬንገር

የጨዋታ ቁጥራዊ መረጃዎች

  • ኮሎኝ በአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዋንጫ ውድድር ላይ ሶስት ጊዜ ለፍፃሜ መብቃት ችሏል። በቅርብ ጊዜ ለፍፃሜ የደረሰውም በ1989/90 ነበር።
  • ኮሎኝ ከአርሴናል ጋር በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታው እስከጨዋታው አጋማሽ ድረስ 1ለ0 መምራት ችሎ የነበረ ቢሆንም የመጨረሻ ውጤቱ ግን በ3ለ1 ሽንፈት አጠናቋል።
  • ለቤሊ ፍየሎቹ ይህ በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው የአውሮፓ ውድድር ተሳትፏቸው ነው።
  • የኮሎኝ ተጭዋች የሆኑት ማርኮ ሆገር እና ክርስቲያን ክሌመንስ ከአርሰናሉ ሲኣድ ኮላሲናች ጋር በሻልከ በጋራ ተጫውተዋል።
  • የፒተር ስቶገር ልጆች በዚህ የውድድር ዘመን በዩሮፓ ሊግ በሜዳቸው ካደረጓቸው ጨዋታዎች አንድ ጨዋታ ሲያሸንፉ አንድ ጨዋታ ላይ ደግሞ ሽንፈት ገጥሟቸዋል።
  • አርሰናል ከወዲሁ ቀጣዩን ዙር መቀላቀሉን ያረጋገጠ ሲሆን የምድቡ ቀዳሚ ለመሆንም የሚያስፈልገው አለመሸነፍ ብቻ ነው። 


ሌሎች የዛሬ ምሽት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች


  አስታና 03 : 00 ቪያሪያል
  ሉጋኖ 03 : 00 ሃፖል ቢር ሼቫ
  ቪክቶሪያ ፕሌዘን 03 : 00 ኤፍሲኤስቢ
  ኦስቴርሰንድስ 03 : 00 ዞርያ
  አትሌቲክ ክለብ 03 : 00 ኸርታ በርሊን
  ባቴ ቦሪሶቭ 03 : 00 ኽሬቭና ዝቬዝዴ
  ኮሎኝ 03 : 00 አርሰናል
  ኮንያስፖር 03 : 00 ማርሴ
  ሳልዝበርግ 03 : 00 ቪቶሪያ ጊዩማሬስ
  ኒስ 03 : 00 ዘልቴ ዋርገም
  ላዚዮ 03 : 00 ቪትስ ኸርነም
  ዜኒት 03 : 00 ቫርዳር
  ሮዘንበርግ 03 : 00 ሪያል ሶሴዳድ
  ሎኮሞቲቭ ሞስኮ 03 : 00 ኮፐንሃገን
  ማከቢ ቴሌ አቪቭ 05 : 05 ስላቪያ ፕራግ
  ስኬንደርቡ ኮርቼ 05 : 05 ዳይናሞ ኪየቭ
  ፓርቲዛን 05 : 05 ያንግ ቦይስ
  ሚላን 05 : 05 ኦስትሪያ ቪየን
  ኤኢኬ አቴንስ 05 : 05 ሪጄካ
  ኤቨርተን 05 : 05 አትላንታ
  ሊዮን 05 : 05 አፖሎን
  ስፖርቲንግ ፕራጋ 05 : 05 ኾፈኒየም
  ሉዶጎሬትስ 05 : 05 ኢስታንቡል ባሳክሴሂር
  ሸሪፍ 05 : 05 ዝሊን

Advertisements