ሰበር ዜና ፦ ሊዮኔል ሜሲ የባርሴሎና ቆይታውን እስከ 2021 አራዘመ

የአምስት ጊዜ የአለም ኮከብ ተጫዋች ስያሜ አሸናፊው አርጀንቲናዊ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በካታላኑ ክለብ ያለውን ቆይታ እስከ 2021 ያራዘመ ሲሆን ለውል ማፍረሻም 700 ሚልዮን ዩሮ ተለጥፎበታል፡፡

እኤአ በ 2000 የ13 አመት ታዳጊ እያለ የካታላኑን ታላቅ ክለብ የተቀላቀለው ሜሲ በቀጣዩ ክረምት ነባሩ የባርሴሎና ውል የሚያልቅ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ መላ ምቶች ሲሰነዘሩበት ቢቆዩም ለልጅነት ክለቡ ያለውን ታማኝነት ድጋሚ በማስረገጥ ውሉን ማራዘም ችሏል፡፡

ሜሲ በአዲሱ ውል መሰረት በካምፕ ኑው የሚኖረውን ቆይታ ወደ 21 አመታት አራዝሞታል፡፡

ኮከቡ ለክለቡ እስካሁን 602 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን 523 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል ፤ በዚህ ቆይታውም 30 ዋንጫዎችን ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡

Advertisements