የጨዋታ ቅድመ ትንታኔ / ሊቨርፑል ከ ቼልሲ 

ቼልሲ ባሳለፍነው መስከረም በቀድሞ ተጫዋቹ ታድኖ ከሲቲ በነበረው ጨዋታ በኬቨን ዴብሩይ የመሪነት ሚና እጅ ለመስጠት ተገዷል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ቤልጄማዊው ተጫዋች ለምን ክለቡን እንዲለቅ ተፈቀደለት የሚለው ጥያቄን ያስነሳ ሆኖ ሰንብቷል። ዛሬ ምሽትም በአንፊልድ ታሪኩ ተመሳሳይ ሆኖ የስታምፎርድ ብሪጁን ክለብ በቀላሉ በለቀቀው እና ከጣሊያን ክለቦች ቆይታ መልስ ለቀያዮቹ በ 19 ጨዋታ 14 ግቦችን ባስቆጠረው መሀመድ ሳላ አስደናቂ ፍጥነትና ብቃት የሚመራውን ሊቨርፑል ይገጥማል። ቼልሲ ዳግም ዛሬም ለቀድሞ ተጫዋቹ ክለብ እጅ መስጠቱንና እጅ ማሰጡቱን በተመለከተ የምሽቱ ጨዋታ ውጤት ይወስነዋል። የቅድመ ጨዋታ ትንታኔውን በተመለከተ ግን የኢትዮአዲሱ ሚኪያስ በቀለ የጨዋታን ወሳኝ ሁነቶች እንደሚከተለው አዘጋጅቷል። 


ጨዋታው የሚደረግበት ሰአት : ምሽት 2:30

ቦታ : አንፊልድ

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤት : ሊቨርፑል 1-1 ቼልሲ

ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት የሚያገኝበት የቴሌቪዥን ጣቢያ : ሱፐር ስፖርት፣ ቢቲ ስፖርት 1 (በመላው እንግሊዝ) እና ቤን ስፖርት (ለመካከለኛው የእስያ ሀገራትና ሰሜን አፍሪካ)

የጨዋታው ዳኛ : ማይክል ኦሊቨር

በዘንድሮው የውድድር ዘመን የጨዋታው ዳኛ አቋም : ጨዋታ 10፣ ቢጫ 42፣ ቀይ 2፣ በየጨዋታው 4.4 ካርዶች መዘዋል

                              ሊቨርፑል

ተጠባቂ አሰላለፍ : ሚኞሌ፣ ክላቫን፣ ሎቭረን፣ አሌክሳንደር አርሎንድ፣ ሞሬኖ፣ ኩቲንሆ፣ ሄንደርሰን፣ ሚልነር፣ ማኔ፣ ሳላህ፣ ፈርሚኖ

በጨዋታው ላይ መሰለፋቸው የሚያጠራጥር : ካን (ለጨዋታ ብቁ ያለመሆን)፣ ማኔ (ጅማት)፣ ማቲፕ (ብሽሽት)

ጉዳት : ዋርድ (ጀርባ)፣ ክላይን (ጀርባ)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : አአሽድድድ

ስነምግባር : ቢጫ 15፣ ቀይ 1

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ሳላ 9

                                ቼልሲ

ተጠባቂ አሰላለፍ : ኮርትዋ፣ አዝቤሉኬታ፣ ክርስቲንሰን፣ ካሂል፣ አሎንሶ፣ ዛፓኮስታ፣ ባካዮኮ፣ ፋብሬጋዝ፣ ካንቴ፣ ሀዛርድ፣ ሞራታ

በጨዋታው ላይ መሰለፋቸው የሚያጠራጥር : ሞሰስ (ለጨዋታ ብቁ ያለመሆን)

ጉዳት : ባትሱሀይ (ቁርጭምጭሚት)፣ ኬኔዲ (ባት)፣ ሙሶንዳ (ጉልበት)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : ሽሽድድድድ

ስነምግባር : ቢጫ 19፣ ቀይ 3

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ሞራታ 8

Advertisements