ሹም ሽረት / ኤሲ ሚላን ቪቼንዞ ሞንቴላን በማሰናበት የቀድሞ ተወዳጅ ተጫዋቹን በምትክ አሰልጣኝነት ቀጠረ

ኤሲ ሚላን አሰልጣኙን ቪቼንዞ ሞንቴላን በማሰናበት 468 ጨዋታዎች ያደረገለትን የቀድሞ ተጫዋቹን ጄናሩ ጋቱሶን በምትክ አሰልጣኝነት ቀጥሯል።

ባሳለፍነው ክረምት በአዲሱ  ቻይናዊ ባለሀብት ስር ከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥቶ ለመጠናከር ጥረት ሲያደርግ የቆየው የጣሊያኑ ክለብ የበዛ ውጤት ማሽቆልቆል ውስጥ መግባቱ ለአሰልጣኙ መሰናበት ምክንያት ሆኗል።  

ከፊዮረንቲና ጋር በነበረው ጨዋታ ቡድናቸው በጎል አልባ የአቻ ውጤት መጨረሳቸውን ተከትሎ ሞንቴላን ያሰናበቱት ሮሰረኒዎቹም ነውጠኛውን የቀድሞውን የክለቡ ተወዳጅ አማካኝ እና የወጣት ቡድኑ አሰልጣኝ የነበረውን ጋቱሶን በምትክነት መሾማቸው ታውቋል።    

የፋሽን ከተማው ክለብ በሴሪ አው የውጤት ሰንጠረዥ ከመሪው ናፖሊ በ 18 ነጥቦች ርቆ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

Advertisements