ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ የ2017 የካፍ ምርጥ ዳኞች እጩ ውስጥ ተካተተ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን[ካፍ] “በሌሎች ዘርፎች”የ2017 የአፍሪካ ምርጦችን ለመሸለም እጩዎችን ሲያሳውቅ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አልቢተር በአምላክ ተሰማ በዳኞች ዘርፍ እጩ ውስጥ ገብቷል።


በ ዕዮብ ዳዲ

ካፍ በቅርቡ የ2017 የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች እንዲሁም በአፍሪካ የሚጫወቱ የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች እጩ ለእያንዳንዱ 30 ተጫዋቾችን ማሳወቁ ይታወቃል።

አሁን ደግሞ “በሌሎች ዘርፎች”የ 2017 የአፍሪካ ምርጦችን ለመለየት በየዘርፉ እጩዎችን አሳውቋል።

በሌሎች ዘርፎች የተካተቱ

በዚህ ዘርፍ ላይ የተካተቱት የ2017 የሴቶች የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች፣የአመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን[በወንድ እና በሴት]፣የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች፣የአመቱ ምርጥ ዳኛ፣የአመቱ ምርጥ ቡድን እና የአመቱ ምርጥ ዳኛ ናቸው።

በዳኞች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ እጩ ሆነው ከተካተቱት ስድስት ዳኞች ውስጥ አንዱ ሆኗል።

በዚህ ዘርፍ መካተት የቻሉት ሌሎች ዳኞች 

ጊአድ ግሪሺያ [ግብፅ]

ጃኒ ሲካዝዌ [ዛምቢያ]

ማላንግ ዲይዲዩ [ሴኔጋል]

መኸዲ አቢድ ቻሪፍ [አልጄሪያ]

ፓፓ ባካሪ ጋሳማ [ጋምቢያ] ናቸው።

በዳኞች ዘርፍ አሸናፊው የሚለየው በካፍ የዳኞች ኮሚቴ ምርጫ መሰረት ሲሆን አሸናፊው በፈረንጆቹ  ሀሙስ ጥር 4 /2018 በጋና አክራ ይታወቃል።

በአምላክ ተሰማ በ 2018 የአለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው ከሚሳተፉ ዳኞች መካከል አንዱ ለመሆን በአቡዳቢ ስልጠና እየወሰደ የሚገኝ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያን በአለም ዋንጫው ወክሎ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል።


በምርጥ ክለቦች እጩ ውስጥ የገቡት አምስት ሲሆኑ እነሱም 

ዊዳድ ካዛብላንካ[ሞሮኮ]

አል አህሊ[ግብፅ]

ቲፒ ማዚምቤ[ዲ ኮንጎ]

ምባኔ ስዋሎውስ [ስዋዚላንድ]

 ሱፐር ስፓርት ዩናይትድ[ደ/አፍሪካ] ናቸው።

ከእጩዎቹ ውስጥ የአመቱ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ዊዳድ ካዛብላንካ ወይንም ለሁለት አመት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማሸነፍ ከቻለው ቲፒ ማዚምቤ አንዱ አሸናፊ እንደሚሆን ይጠበቃል። 


ከአሰልጣኞች ደግሞ

ገርኖት ሮሆር [ናይጄሪያ]

ሄክቶር ኩፐር [ግብፅ]

ሁጎ ብሩስ [ካሜሮን]

ሚሀዬ ካዚምቤ[ቲፒ ማዚምቤ]

ሁሴን አሞታ[ዊዳድ ካዛብላንካ] ሆነዋል።

Advertisements