የቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ 16 የጥሎማለፍ ተፋላሚዎች የእጣ ድልድል መቼ ይወጣል ?

1.jpg

በዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ምንም እንኳን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ቢቀሩም አብዛኛዎቹ ታላላቅ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል፡፡አንዳንዶቹ ደግሞ ከምድባቸው ሁለተኛ ሆነው የማጠናቀቅ እድል ስላላቸው ከወዲሁ 16ቱ ቡድኖች የሚያደርጉት የጥሎማለፍ ጨዋታዎች ማን ከማን ያገናኛል የሚለው ተጠባቂ ሆኗል፡፡ለመሆኑ የጥሎማለፉ የእጣ ማውጣት ስነስርአቱ መቹ ይካሄዳል?

እንደ ማንችስተር ሲቲ፣ቶተንሀም፣ፒ ኤስ ጂ እና ባየርሙኒክ አይነት ቡድኖች ከወዲሁ ማለፋቸውን ማረጋገጥ ሲችሉ ሴልቲክ፣አንደርሌክት እና ፌይኖርድ ደግሞ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድላቸው አክትሟል፡፡ነገርግን ከምድባቸው ሶስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ እድል ስላላቸው በዩሮፓ ሊግ ላይ የመሳተፍ እድል ይኖራቸዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ በመጨረሻው ጨዋታ ላይ የሚያስመዘግቡት ውጤት ታይቶ ከምድባቸው ሶስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ ከቻሉ እነ አርሰናል ወደ የሚገኙበት ዩሮፓ ሊግ ይቀላቀላሉ፡፡ዘንድሮ በዩሮፓ ሊጉም ቢሆን ጠንካራ ፉክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ለዚህ ደግሞ በዘንድሮ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ከምድባቸው የማለፍ እድላቸው እጅግ የጠበበ እድል ያላቸው ታላላቅ ቡድኖች ወደ ዩሮፓ ሊግ መቀላቀላቸው እንደማይቀር ተገምቷል፡፡

1

በቻምፒየንስ ሊጉም ወደ ቀጣዩ 16 የሚቀላቀሉ ቡድኖች በጥሎ ማለፍ የሚገጥሟቸውን ቡድኖች በስዊዘርላንድ ኒዮን በፈረንጆቹ ሰኞ ታህሳስ 11 ላይ በሚወጣው እጣ ማውጣት ስነ ስርአት የሚታወቅ ይሆናል፡፡

እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአንድ ምድብ ላይ የነበሩ ቡድኖች እና የአንድ ሀገር ቡድኖች እርስ በርስ የመገናኘት እድል አያገኙም፡፡ምድባቸውን በአንደኝነት ያጠናቀቁ ቡድኖች ደግሞ የጥሎ ማለፉን የመልስ ጨዋታ በሜዳቸው የማድረግ እድል ያገኛሉ፡፡

የመጀመሪያ ጨዋታዎችም በፈረንጆቹ የካቲት 13/14 እንዲሁም የካቲት 20/21 ሲደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ መጋቢት 6/7 እንዲሁም መጋቢት 13/14 ተደርገው ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚቀላቀሉ ቡድኖች ይለያሉ፡፡

 

 

Advertisements