የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ 11

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ለክለቦቻቸው ውጤታማነት ከፍ ያለ አቅማቸውን አማሳየት የቻሉ ምርጥ 11 ተጫዋቾችን እንደሚከተለውን ተመልክተናቸዋል።

የተጫዋቾች ምርጫ ዝርዝሩን የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ነው።

1. መሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

የቀድሞው ክለቡን የገጠመው ግብፃዊው ተጫዋች በተጠናቀቀው ሳምንትም ለሊቨርፑል በፕሪሚየር ሊጉ ባዳረጋቸው 13 ጨዋታዎች 10ኛ ግቡን በሰማያዊዎቹ ላይ አንድ ግብ በማስቆጠር ጫፍ የደረሰ ብቃት ያለው አጥቂ መሆኑን አስመስክሯል።

2. ሉካስ ፋቢያንስኪ (ስዋንሲ)

ቅዳሜ በ13ኛው ሳምንት ጨዋታ ከፕሪሚየር ሊጉ የትኞቹም ግብ ጠባቂዎች በላይ አምስት የግብ ሙከራዎችን በማዳን ባተሌ ሆኖ ነበር ያሳለፈው። ይህ ብቃቱም ስዋንሲ ግብ ሳይቆጠርበት ከቦርንማውዝ ጋር በአቻ ውጤት እንዲያጠናቅቅ አስችሎታል።

3. ኪራን ትሪፐር (ቶተንሃም) 

ትሪፐር በሳምንቱ መጨረሻ ከየትኛውም ተጫዋች በላይ ሰባት የግብ ማስቆጠር ዕድሎችን መፍጠር ችሏል። ይሁን እንጂ ስፐርስ በሜዳው አንድ ግብ ብቻ በማስቆጠር ከዌስት ብሮም ጋር 1ለ1 በሆነ ውጤት በመለያየቱ ጥረቱ ያን ያህልም ከፍ ያለ ዋጋ አልነበረውም።

4. አንድሬያስ ክርስቲያንሰን (ቼልሲ)

ተከላካዩ 96 በመቶ ስኬታማ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ከማቀበሉም በላይ ኃይለኛው የሊቨርፑል አጥቂ ክፍል የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እና በአንፊልድ አንድ ግብ ብቻ እንዲያስቆጥር አስገድዶታል።

5. ላውረንት ኮቪየልኒ (አርሰናል)

ኮሺየልኒ ከበርንሌይ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሁለት የግብ ዕድሎችን መፍጠር የቻለ ሲሆን፣ በሳምንቱ ጨዋታ በአንድ ጨዋታ ላይ ከፍተኛውን ስምንት የግብ ዕድሎችን በማምከን አርሰናል በከባድ ትግል በርንሌይ 1ለ0 እንዲያሸንፍ ማድረግ ችሏል።

6. ማማዱ ሳኮ (ክሪስታል ፓላስ)

ተከላካዩ የፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛውን ከየካቲት 2016 ወዲህ ደግሞ የመጀመሪያውን የሆነውን ግብ ማስቆጠር ችሏል። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ያስቆጠራት ግብ ስቶክ ሲቲን 2ለ1 ማሸንፍ ያስቻለቻቸውን የጭማሪ ሰዓት ግብ ነበር።

7. ፒየር-ኢሚል ሄይብየርግ (ሳውዛምፕተን)

ተጫዋቹ በጨዋታው ላይ ከፍተኛ የተባለውን 96 ኳሶችን ያቀበለ ሲሆን በውጤት ማጣት መንገታገት ላይ የሚገኘውን ኤቨርተንን 4ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉም ያደረጋቸው የኳስ ቅብብሎሽ 92 በመቶዎቹ ስኬታማ ነበሩ።

8. ፈርናንዲንሆ (ማንችስተር ሲቲ)

ፈርናንዲንሆ በሳምንቱ መጨረሻ  ሶስተኛው ከፍተኛ የሆነ በድምሩ 104 ኳሶችን ማቀበል ችሏል። ከእነዚህ ኳሶችም 93 በመቶ ያህሉት ኸደርስፊልድን 2ለ1 እንዲያሸንፉ ያስቻሉ በትክክል የቡድን አጋሮቹ ጋር መድረስ የቻሉ ኳሶች ነበሩ።

9. ኸርዳን ሻኪሪ (ስቶክ ሲቲ)

ኸርዳን ሻኪሪ ክለቡ ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች በተቆጠሩት ስድስት ግቦች ላይ የእሱ እጅ አለበት (ሁለት ሲያስቆጥር፣ አራቱን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል)።  ከእነዚህም መካከል ስቶክ ቅዳሜ ዕለት ያስቆጠረውን የጨዋታው የመጀመሪያ ግብንም ያካትታል። ይሁን እንጂ ስቶክ በክሪስታል ፓላስ 2ለ1 ተሸንፏል። 

10. ዱሳን ታዲች (ሳውዛምፕተን)

ታዲች ሳውዛምፕተን እሁድ ኤቨርተንን ባሸነፈበት ጨዋታ አንድ ግብ ከማስቆጠሩም በላይ አንድ የግብ ዕድልም መፍጠር ችሏል። ተጫዋቹ ቅዱሳኑን ነሃሴ 2014 ከተቀላቀለበት ጊዜ አንስቶ ከየትኞቹም የክለቡ ተጫዋቾች በላቀ 41 የፕሪሚየር ሊግ ግቦችን እንዲየስቆጥሩ የራሱን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል (16 ሲያስቆጥር 25 ግቦችን ደግሞ አመቻችቷል።)

11. ቻርሊ ኦስቲን (ሳውዛምፕተን)

ቻርሊ ኦስቲን ሳውዛምተን በኤቨርተን ላይ የበላይ ሆኖ እንዲያሸንፍ ትልቁን ሚና ተጫውቷል። አጥቂው ለክለቡ የመጀመሪያ ተሰላፊ ሆኖ መጫወት በቻለባቸው ያለፉት 11 ጨዋታዎች ላይ ስምንት ግቦች እንዲያስቆጥሩም የራሱን ሚና ተጫውቷል (ሰባቱን ሲያስቆጥር አንዱን ደግሞ አመቻችቷል)

Advertisements