ሳኡዲ አረቢያ የቀድሞውን የቺሊ አሰልጣኝ ቀጠረች

ሳኡዲ አረቢያ ኤድጋርዶ ባኡዛን ከአሰልጣኝነት ኃላፊናታቸው ካሰናበተች በኋላ የቀድሞውን የቺሊ አሰልጣኝ የነበሩትን ኹዋን አንቶኒዮ ፒዛን የብሔራዊ ቡድኗን በ2018 የዓለም ዋንጫ በአሰልጣኝነት እንዲመሩ በማሰብ ቀጥራለች።

የቀድሞው የአርጄንቲና አሰልጣኝ ቡኣዛ ብሔራዊ ቡድኑ በወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ከመሩ በኋላ ከአስልጣኝነት ሚናቸው የተነሱት ባለፈው ሳምንት ነበር።

ትውልደ አርጄንቲናዊ የሆኑት አዲሱ አሰልጣኝ ፒዚ በሮዛሪዮ፣ ቴነሪፌ፣ ቫሌንሺያና ባርሴሎና ክለቦች ውስጥ እንዲሁም ለስፔን ብሄራዊ ቡድን በአጥቂነት መጫወት የቻሉ ሲሆን አሁን ዳግሞ የቡኣዛ ምትክ ሆነው የሳኡዲ አረቢያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ሚናን ተረክበዋል።

ሳውዲ አረቢያ አርብ በሞስኮው ክሪምሊን ቤተመንግስት ይፋ በሚሆነው የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት የምድብ ተጋጣሚዎቿን የምታውቅ ይሆናል።

Advertisements