ኤቨርተን ሳም አላርዳይስን አዲስ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጠረ

ባለፈው ወር ሆለንዳዊውን አሰልጣኝ ያሰናበተው ኤቨርተን የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኙን እና በዚህ የውድድር ዘመን ከክሪስታል ፓላስ የተሰናበቱትን ሳም “ቢግ ሳም” አላርዳይስን በአሰልጣኝነት መቅጠሩን በይፋዊ ደረገፁ ባወጣው መግለጫ ገልፅዋል።

ክለቡ በመግለጫው አክሎም ኤቨርተን ዛሬ ምሽት ዌስት ሃምን በጉዳሰን ፓርክ ሲገጥም ከኮማን ስንብት በኋላ ክለቡን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሲመሩት በቆዩት ምክትል አሰልጣኙ ዴቪድ አንስዎርድ እየተመራ ጨዋታውን እንደሚያደረግም ገልፅዋል።

ሳሙኤል አላርዳይስ ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ኃላፊነታቸው በተጨማሪ በ1991 በሊመሪክ ወደአሰልጣኝነት ስራ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ እንደቦልተን፣ ኒውካሰል፣ ብላክበርን፣ ዌስት ሃም ዩናይትድ፣ ሰንዳርላንድና ክሪስታል ፓላስ ያሉ አበይት የእንግሊዝ ክለቦችን ማሰልጠን ችለዋል።

Advertisements