የዛሬ ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ቅኝት

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ14ኛው ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ ቀን ዛሬ [ረቡዕ] በተቀመጠላቸው የጨዋታ መርሃግብር መሰረት ስድስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ኢትዮአዲስ ስፖርትም ከምሽት 4፡45 አንስተው የሚካሄዱትን ስድስት ጨዋታዎች ላይ በሙሉ እንደሚከተለው ቅደመ ዳሰሳ አድርጋለች።

ቦርንማውዝ ከ በርንሌይ

የቦርንማውዝ የቡድን ዜናዎች: አምበሉ ሲሞን ፍራንሲስ የነበረበትን የአንድ ጨዋታ ቅጣት ጨርሶ በዚህ ጨዋታ ላይ ይሰለፋል። ጀርሜን ዴፎ (በባት ጉዳት)፣ እና ጁኒየር ስታኒስላስ (በብሽሽት ጉዳት) ቅዳሜ ከስዋንሲ ሲቲ ጋር ያለግብ አቻ የተለያዩበት ጨዋታ ያለፋቸው ተጫዋቾች ናቸው። ብራድ ስሚዝ (በዳሌ ጉዳት) እና ትይሮኔ ሚንግስ (በጀርባ ጉዳት) አሁንም  ያላገገሙ ተጫዋቾች ናቸው።

አሰልጣኙ ኤዲ ሃው ስለጨዋታው: “ተጫዋቾቹ በራስ መተማመን ለመጫወት በጥሩ የአዕምሮ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በብርሃናማዎቹ ፊት በሜዳችን መጫወትንም የምንወደው ነገር ነው። ለመጨረሻ ጊዜ በሜዳችን ከኸደርስፊልድ ጋር ስንጫወት እንዳደረግነው የግብ ሂሳባችንን በጥሩ ሁኔታ መክፈትም እንሻለን።”

የበርንሌይ የቡድን ዜናዎች: ማት ዳውሰን ቀላል በሚባል የግጭት ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፉ ሲያጠራጥር፣ ፊል ባርድስሌይ ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላይነት ስፍረውን ለመረከብ ዝግጁ ነው። ክሪስ ዉድ በአሽሊ ባርነስ ምትክ ወደፊት ለፊት የመጫወቻ ቦታው ሊመለስ ይችላል። ነገር ግን ዲን ማርኔይ እና ጆን ዋልተርስ (ሁለቱም በጉልበት ጉዳት)፣ እንዲሁም ቶም ሂተን (በትከሻ ጉዳት) በዚህም ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

አሰልጣኙ ሺን ዳይች ስለጨዋታው: “እነሱ ጥሩ ቡድን ናቸው። ኤዲንም ሆነ በተጫዋቾቹ የሰራውን ነገር በጣም አከብርለታለሁ። በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥም እንኳ ቢሆን እንደቡድን በጋራ ሆነው ይታያሉ። እኛም በዚህ ነገር ላይ ጥሩ ነን። በተሻለ ብልህ መሆንም ችለዋል። ጥሩ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል፤ እሱም ወደፊት መጓዙን ቀጥሏል።”

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤት: ቦርንማውዝ 2 በርንሌይ 1 ፣  በርንሌይ 3 ቦርንማውዝ 2

ያለፉት አምስት የሊግ ጨዋታ ውጤቶቻቸው: ቦርንማውዝ ድል ሽን ድል ድል አቻ፣ በርንሌይ ሽን ድል ድል ድል ሽን

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች: ካሊዩም ዊልሰን (ቦርንማውዝ) 4፣ ክሪስ ዉድ (በርንሌይ) 5

የጨዋታው ዳኛ: ሮጀር ኢስት (ከዊልትሻየር)

አርሰናል ከ ኸደርስፊልድ

የአርሰናል የቡድን ዜናዎች: በሳምንቱ መጨረሻ ቀን በርንሌይን 1ለ0 በረቱበት ጨዋታ ላይ በህመም ምክኒያት ያልተሰለፈው መሱት ኦዚል በዚህ ጨዋታ ወደሜዳ እንደሚመልስ ይጠበቃል። አሌክስ አይዎቢ በእግር ጉዳት ምክኒያት አለመስለፉ እርግጥ ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የሚገኘው ሳንቲ ካዛሮላም በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ተጫዋች ነው። ከሁለቱ ውጪ አርሰናል ሌላ ይፋ የሆነ የጉዳት ችግር የለበትም።

አሰልጣኙ አርሰን ቬንገር ስለጨዋታው : “በጣም ትልቅ ጨዋታ ነው። ምክኒያቱም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ተመልክቼዋለሁ። መሸነፍ አልነበረባቸውም። ያን ቡድን በሙሉ ይዘው ሲገቡ በተለይም የመጀመሪያው የውድድር ዘመናቸው እንደመሆኑ አደገኛ ያደረጋቸውን ያን አይነቱ የፍልሚያ መንፈስ ትገነዘባለህ።”

የኸደርስፊልድ የቡድን ዜናዎች: ራጂቭ ቫን ላ ፓራ እሁድ በማንችስተር ሲቲ በተሸነፉነት ጨዋታ ላይ ቀይ ካርድ በመመልከቱ በቅጣት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ አይሰለፍም። ካሲ ፓልመር ከረጅም ጊዜያት ከሜዳ ካራቀው የቋንጃ ጉዳት አገግሞ ወደሜዳ ለመመለስ የተቃረበ ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ላይ ግን አይሳተፍም።

አሰልጣኙ ዴቪድ ዋግነር ስለጨዋታው: “አርሰናል በሜዳው ላይ ያስመዘገባቸውን ውጤቶችም ሆነ እኛ ከሜዳችን ውጪ ያስመዘገብናቸውን ውጤቶች ሁሉም ያውቃል። በደረጀችን ከፍ ብለን አለመገኘታችን የዕድል ጉዳይ ይመስላል።  ነገር ግን ጨዋታው ሲጀምር ይህ ከቁጥር ውስጥ አይገባም። ከዚህ ጨዋታ አንዳች ነገር ለማግኘት የምንችለውን ነገር በሙሉ እናደርጋለን።”

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤቶቻቸው: አልተገኛኙም

ባለፉት አምስት ጨዋታዎቻቸው ያስመዘገቧቸው ውጤቶ: አርሰናል ድል ድል ሽን ድል ድል፣ ኸደርስፊልድ ድል ሽን ድል ሽን ሽን

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች: አሌክሳንደር ላካዜቴ (አርሰናል) 6፣ ስቲቭ ማውኔ፣ አሮን ሙይ፣ እና ላውረንት ደፖይትሬ (ኸደርስፊልድ) 2

የጨዋታው ዳኛ : ግርሃም ስኮት (ከኦክስፎርድሻየር)

ቼልሲ ከ ስዋንሲ

የቼልሲ የቡድን ዜናዎች: ዴቪድ ልዊዝ በጉልበት ጉዳት ፣ ሚኪ ባትሹኣዪ በቁርጭምጭሚት ጉዳት፣ ቻርሊ ማሶንዳ በጉልበት ጉዳት እንዲሁም ኬኔዲ ባልተገለፀ ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ሲሆን ቪክቶር ሞሰስ ግን በዚህ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ተሰላፊ ሊሆን ይችላል።

አሰልጣኙ አንቶኒዮ ኮንቴ: “ተጫዋቾቼ ለቼልሲ በመጫወታቸው ሊደሰቱ ይገባቸዋል። የመጀመሪያ ተሰላፊው ሆነው ጨዋታን ጀምረውም ሆነ በተቀያሪ ወንበር ላይ ሆነው ቢገቡ የግድ ደስተኛ መሆን አለባቸው። እኔም ይህን ሁኔታ የሚረዱና የሚቀበሉ ተጫዋቾች ነው ያሉኝ። አንድ ትልቅ ቡድን ውስጥ ስትጫወት ደግሞ ይህን መቀበል ይኖርብሃል።”

የስዋንሲ የቡድን ዜናዎች: በአባቱ ህልፈት ምክኒያት አርጄንቲናዊው ተጫዋች ፌድሪኮ ፈርናንዴዝ ከቼልሲ ጋር እና ከስቶክ ጋር በሚያደረጓቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ አሰለፍም። እንዲሁም ከቼልሲ በውሰት በመጫወት ላይ የሚገኘው ታሚ አብርሃምም በውል ስምምነቱ መሰረት በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፍ የማይችል ተጫዋች ነው።  

አሰልጣኙ ፓውል ክሌመንት: “ቡድኑ የራስ መተማመኑ ዝቅ የማለቱ ጉዳይ ምንም ዓይነት ሚስጥር የለውም። ነገር ግን [ከቦርንማውዝ ጋር በሚደረገው ጨዋታ] ውድድሩና ፍልሚያው ጠንካራ ነው። እኛም ጥሩ እግርኳስ እንጫወታለን። ከዚህ ቀደም ከነበርንበት አቋም የተለየን ሆነን እንደምንቀርብም እጠብቃለሁ።”

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤታቸው: ቼልሲ 3 ስዋንሲ 1፣ ስዋንሲ 2 ቼልሲ 2

ያለፉት አምስት ጨዋታ ውጤቶቻቸው: ቼልሲ ድል ድል ድል ድል አቻ፣ ስዋንሲ ሽን ሽን ሽን ሽን አቻ

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች: አልቫሮ ሞራታ (ቼልሲ) 9፣ ታሚ አብርሃም (ስዋንሲ) 5

የጨዋታው ዳኛ: ኒል ስዋርብሪክ (ከላንክሻየር)

ኤቨርተን ከ ዌስትሃም


የኤቨርተን የቡድን ዜናዎች
: ሌይተን ቤንስ እና ማይክል ኬን እሁድ ከሳውዛምፐተን ጋር በተደረገው ጨዋታ በጉዳት ምክኒያት ጨዋታ አቋርጠው መውጣታቸውን ተከትሎ በዚህ ጨዋታ ላይም የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው። ማሰን ሆልጌት በብሽሽት ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ሲሆን፣ ኦማር ናያሲ በቅጣት ምክኒያት የማይሰለፍ ሌላኛው ተጫዋች ነው። ቶም ዴቪስ ግን የነበረበትን ቅጣት ጨርሶ ለዚህ ጨዋታ ወደሜዳ የሚመለስ ይሆናል።

አሰልጣኙ ዴቪድ አንስዎርዝ: “ቡድኑ በወረደ ብቃት ውስጥ ይገኛል። በፍጥነት ማሸነፍ መጀመር ይጠበቅብናል። በህብረት መሆን እና ተጫዋቾቹ በተጠንቀቅ አቅማቸውን ማሳየት አለባቸው። ድፍረትና የአዕምሮ ጥንካሬም ያስፈልገናል። የግድ ማሸነፍ ያለብንም ጨዋታ ነው።”

የዌስት ሃም የቡድን ዜናዎች: ማርኮ አርናቶቪች ምንም እንኳ አርብ ምሽት ከሌስተር ጋር 1ለ1 በተለያዩበት የጨዋታ ማብቂያ እያነከሰ ቢወጣም በዚህ ጨዋታ ላይ ግን የሚሰለፍ ይሆናል። ነገር ግን  ኻቪየር ኸርናንዴዝ፣ ሚካኤል አንቶኒዮ (ሁለቱም በቋንጃ) ጉዳት እና ጄምስ ኮሊንስ (በቁርጭምጭሚት) ጉዳት ምክኒያት ወደጨዋታ ላይ የመመለሳቸው ነገር እርግጥ አይደለም።

አሰልጣኙ ዴቪድ ሞየስ: “ለሆደ ባሻነት ቦታ ይኖረን ይሆን? አይኖረንም። ምክኒያቱም ከዌስትሃም ጋር የግድ ማሸነፍ ይኖርብኛል። በእርግጥም ሶስት ነጥቦችን ለመውሰድ ሙከራ ማድረጋችን ወሳኝ ነገር ነው። ባልፉው ሳምንት የመጀመሪያውን ነጥባችንን አግኝተናል። የመጀሪያው ከግብ የፀዳ ጨዋታ እና የመጀመሪያው ሶስት ነጥብም ያስፈልገናል። ቢያንስ ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንደምናገኝ ተሳፋ አለኝ። 

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤታቸው: ዌስት ሃም 0 ኤቨርተን 0፣ ኤቨርተን 2 ዌስት ሃም 0

ያልፉት አምስት ጨዋታ ውጤቶቻቸው: ኤቨርተን ሽን ሽን ድል አቻ ሽን፣ ዌስት ሃም ሽን አቻ ሽን ሽን አቻ 

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች: ኦማር ናያሴ (ኤቨርተን) 6፣ አንድሬ አየው (ዌስት ሃም) 5 

የጨዋታው ዳኛ: ማይክል ኦሊቨር (ከኖርዘምበርላንድ)

ማን ሲቲ ከ ሳውዛምፕተን

የማን ሲቲ የቡድን ዜናዎች: ጆን ስቶንስ (በቋንጃ) እና ቤንጃሚን  ሜንዲ (በጉልበት) ጉዳቶች አሁንም ከሜዳ እንደራቁ ይቆያሉ። በቅርቡ ከቋንጃ ጉዳት የተመለሰው ቪንሰንት ኮምፓኒ በዚህ ጨዋታ ረፍት የሚሰጠው ከሆነ በመሃል ተከላካይነት ቦታ ላይ መሰለፍ የሚችለው ተጫዋች ኢላኪዩም ማንጋላ ብቻ ይሆናል።

አሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ: “በዚህ የውድድር ዘመን ሳውዛምፕተንን ስመለከት በርካታ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። እናም እሱ [ማውሪሲዮ ፔሌግሪኒ] ባለፈው የውድድር ዘመን በአላቬስ ድንቅ ስራ ሰርቷል። [በባርሴሎና] አንድ ወይም ሁለት የውድድር ዘመኖች አብረን ነበርን። አስደናቂ ተመክሮ ያሳለፍኩበት ጊዜ ነበር። ከጨዋታው በኋላም ትንሽ ለማውጋት ጥሩ አጋጣሚ ይኖረናል።” 

የሳውዛምፕተን የቡድን ዜናዎች : ኤቨርተንን 4ለ1 በረቱበት ጨዋታ በቅጣት ምክኒያት መሰለፍ ያልቻለው ኦሪዮል ሮሚዩ ቅጣቱን ጨርሶ ተመልሷል። ከቶፊሶቹ ጋር በተደረገው ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ በቁርጭምጭሚት ጉዳት ከሜዳ የወጣው ማሪዮ ለሚና ከጉዳቱ የተመለሰ ሲሆን፣ ማት ታርጌት ግን አሁንም [በእግር ጉዳት] ከሜዳ እንደራቀ ይቆያል።

አሰልጣኙ ማውሪሲዮ ፔሌግሪኖ : “በእግርኳስ እና በስፖርት ላይ የማይሸነፍ ማንም የለም።  እያንዳንዱ ቡድን ችግሮች አሉበት። ምክኒያቱም ኸደርስፊልድ የሆነ ነገር ለማግኘት ተቃርቦ ነበር። ዕድል ማግኘት የምንፈልግ ከሆነ የበላይ ሆነን መገኘት ይጠበቅብናል። ጥሩ ቀን እንደሚሆንልንም ተስፋ አለኝ።”

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤታቸው: ሳውዛምፕተን 0 ማን ሲቲ 3፣ ማን ሲቲ 1 ሳውዛምፕተን 1

ያላፉት አምስት የሊግ ጨዋታ ውጤቶቻቸው:  ማን ሲቲ ድል ድል ድል ድል ድል፣ ሳውዛምፕተን ድል አቻ ሽን ሽን ድል

ከፈተኛ ግብ አስቆጣሪዎች: ራሂም ስተርሊንግ (ማን ሲቲ) 12፣ ማኖላ ጋቢያዲኒ፣ ስቴቨን ዴቪስ እና ቻርሊ ኦስቲን (ሳውዛምፕተን) 3

የጨዋታው ዳኛ: ፓውል ቲረኒ (ከላንክሻየር)

ስቶክ ከ ሊቨርፑል

የስቶክ የቡድን ዜናዎች: በክሪስታል ፓላስ ሲሸነፉ የቁርጭምጭሚት ግጭት ገጥሞት የነበረው ራማዳን ሶብሂ ወደጥሩ አቋሙ ተመልሷል። ሳይዶ በራሂኖ በ13ኛው ሳምንት ጨዋታ ላይ ባይሰለፍም በዚህ ጨዋታ ላይ ግን ወደሜዳ እንደሚመለስ ይጠበቃል። ጂኦፍ ካሜሮን (በየአጥንት መናጋት ጉዳት) እና ጃክ በትላንድ (በጣት ጉዳት) አሁንም ከጨዋታ እንደራቁ የሚቆዩ ተጫዋቾች ናቸው።

አሰልጣኙ ማርክ ሂዩዝ: “የተናጥልና እና የጋራ ስህተቶች ባለፈው ሳምንት እንድንረታ አድርገውናል። ጉዳያችንም እነዚህን ነገሮች መቅረፍ ነው። አንድ ጊዜ ያን በሚገባ ከለየን (ደግሞም የለጥርጥር እናደርገዋለን) ጥሩ እንሆናል። ምክኒየቱም የብቃት ደረጃችን መልካም ነው። የተሳሳተ ነገር ለማድረግ ብዙ እንሰራለን ብዬ አላስብም።” 

የሊቨርፑል የቡድን ዜናዎች: ከቼልሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ያልተሰለፉት ሳዲዮ ማኔ እና ሮቤርቶ ፊርሚኖ ለዚህ ጨዋታ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው። እነሱን ተክተው የተጫወቱት አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን እና ዳንኤል ስተርጂ ደግሞ በዚህ ጨዋታ ላይ የመሰለፋቸው ዕድል ዝቅተኛ ይመስላል። የደያን ሎቭረን የመሰለፍ ገዳይ ደግሞ ዘግይቶ በሚሰጥ ውሳኔ የሚታወቅ ይሆናል።

አሰልጠኙ የርገን ክሎፕ: “እነሱ [ማንችስተር ሲቲዎች] ማሸነፍ ካቆሙ እና የእኛ ቡድን ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ከሆነ ልትደርስባቸው የመቻለህ ነገር እውን ሊሆን ይችላል። እኛ ቀጣዩን ሶስትት ነጥቦች እንፈልጋቸዋለን። ከዚያም የሚቀጥሉትን እንዲሁም የሚቀጥሉትን ሶስት ነጥቦች። ምክኒያቱም የሚቸገር ካለ ያን ጊዜ እሱ ላይ መድረስ ይጠበቅብናል።” 

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤታቸው: ስቶክ 1 ሊቨርፑል 2፣ ሊቨርፑል 4 ስቶክ 1

ያለፉት አምስት የሊግ ውጤቶቻቸው: ስቶክ ሽን ድል አቻ አቻ ሽን፣ ሊቨርፑል ሽን ድል ድል ድል አቻ

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች: ፒተር ክራውች (ስቶክ) 4፣ መሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል) 15

የጨዋታው ዳኛ: ማርቲን አትኪንሰን (ምዕራብ ዮርክሻየር)

Advertisements