ናፖሊ ከ ጁቬንቱስ | የሴሪ አ ጨዋታ ቅድመ ቅኝት

​​


በ15ኛ ሳምንት በውድድር አመቱ ተጠባቂ በሆነው የጣልያን ሴሪ አ ጨዋታ ናፖሊን ከ ዩቬንቱስ በስታድዮ ሳን ፓውሎ 
ምሽት 4:45 ያገናኛል። ፓርቴኖፒዎቹ (ናፖሊዎች) በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ተቀመጠው በ14 ጨዋታ ያለመሸነፍ ጉዟቸውን ለማስቀጠል ሲጫወቱ ተጋጣሚያቸው የዕድሜ አዛውንቷ ደሞ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ትጫወታለች።


ባለሜዳው ናፖሊ14 ጨዋታዎችን ያልተሸነፈ ሲሆን 12 ጨዋታዎችን አሸንፎ 2 አቻ ወቶ ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ በ38 ነጥብ በሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል። አስፈሪ የአጥቂ ክፍል ያለው ናፖሊ በመጨረሻዎቹ አስር ጨዋታዎች ስምንት ጎሎችን አስቆጥሯል። የሳሪው ናፖሊ በአውሮፓ ከአብላጫ የኳስ ቁጥጥር ጋር ማራኪ እግር ኳስን ከሚጫወቱ ክለቦች መካከል አንዱ ነው ። ናፖሊ በሜዳው ጥሩ ሪከርድ ያለው ሲሆን ከኢንተር ሚላን ጋር አቻ ከመውጣቱ ውጪ ሁሉንም የሜዳ ጨዋታዎቹን አሸንፏል። በመጨረሻ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎቹ 17 ጎሎችን ሲያስቆጥር ሶስት ግቦች ብቻ ተቆጥረውበታል።

ናፖሊ

Napoli

የቡድን ዜናዎች

ማውሪዚዮ ሳሪ በግራ መስመር ተከላካዮቻቸው ፋኡዚ ግሁለም እና በመሃል አጥቂው አርካዲዩስ ሚሊክ ላይ ያለው ረጅም ጊዜ የዘለቀ የጉልበት ጉዳት አሁንም የቡድናቸው አብይ ችግር ነው።

ቁልፍ ተጫዋች

በዚህ ጨዋታ ላይ በቁልፍ ተጫዋችነት ልንመለከተው የሚችለው ተጫዋች ድሪስ መርተንስ ነው። ጎንዛሎ ሄጉዌን ክለቡን ለቆ ሲወጣ ብዙዎች የቡድኑን ዘላቂ ብቃት ተጠራጥረው ነበር። ይሁን እንጂ ቤልጂየማዊውን የክንፍ ተጫቃች ወደአጥቂ ስፍራ ከዛወሩት በኋላ ወዲያውኑ ከቡድኑ ጋር መዋሃድ ችሏል። እናም ይህ ተጫዋች በዚህ ጨዋታ ከበታቻቸው የሚገኘውን ጁቬንቱስን አሸንፈው ለዋንጫው የሚያደርጉትን ፉክክር እንደሚያስቀጥል ይጠበቃል። ተጫዋቹ በሁሉም ውድድሮች ላይ ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 13 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ዘጠኝ የግብ ዕድሎችን ደግሞ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ይህ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የተሟላ ብቃት ካላቸው አጥቂዎች ተርታ የሚያልሰፈው ነው።

የቡድኑ ወቅታዊ ውጤቶች

ናፖሊ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሶስቱን ሲያሸንፍ፣ አንዱን በአቻ ውጤት አንዱን ደግሞ በሽንፈት አጠናቋል።

0-1 ዩዴኒዚን አሸነፈ
3-0 በሻምፒዮንስ ሊጉ ሻልከን በሜዳው አሸነፈ
2-1 ኤሲ ሚላንን በሜዳው አሸነፈ
0-0 ከሼቮ ጋር በአቻ ውጤት አጠናቀቀ
2-4 በሻምፒዮንስ ሊጉ በሜዳው በማን ሲቲ ተሸነፈ 

ጁቬንቱስ

Juventus

የቡድን ዜናዎች

ማሲሚላኖ አሌግሪ የታፋ ጉዳት ችግር ያለበት የመሃል ተከላካዩን ጆርጂዮ ቸሊኒን የማሰለፋቸው ነገር አናሳ ነው። ሌችተንስታይነርና ኳድራዶም በጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ናቸው። የማንዙጊችም መግባት አጠራጣሪ ነው። ይህም የአሮጊቷን የማጥቃት ሀይሉን ያሳሳዋል ተብሎ ይጠበቃል። አጥቂው ጎንዛሎ ሄጉዌንም ስብራት የገጠመውን ጣቱን በቅርቡ ቀዶ ህክምና ማድረጉን ተከትሎ የመሰለፉ ነገር “50-50” ነው።

ቁልፍ ተጫዋች

አዛውንቷ ጎንዛሎ ሄጉዌንን ከናፖሊ ካስፈረመች ጊዜ አንስቶ ከኔፕልሱ ክለብ ጋር በቀላሉ የምትላቀቀው ጨዋታ አልገጠማትም። ናፖሊም ሄጉዌንን ቢያጣም ተጫዋቹ ግን አሁንም በጠንካራነቱ ቀጥሏል። በመሆኑም ናፖሊዎች ሄጉዌንን ማጣታቸው ያን ያህልም ሊያስጨንቃቸው የሚገባ አይመስልም። ይሁን እንጂ ተጫዋቹ አሁንም በቀድሞ ብቃቱ ላይ አይገኝም። ከዚህ ጨዋታ በፊት ለመድረስም ቀዶ ህክምና አድርጓል። በመሆኑም በሁሉም ውድድሮች ላይ ባስቆጠራቸው አስር ግቦች ላይ ተጨማሪ ለማከል ከቀድሞ ክለቡ ጋር አለመጫወትን ፈፅሞ የሚያስበው ነገር አይደለም።

ወቅታዊው ውጤቶች

ጁቬዎች ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለት ጨዋታዎችን ሲያሸንፉ፣ ሁለቱን ከአሻ አንዱን ደግሞ በሽንፈት አጠናቀዋል።

3-0 ክሮቶኔን በሜዳቸው አሸነፉ
0-0 በሻምፒዮንስ ሊጉ በሜዳቸው አቻ ተለያዩ
3-2 በሳምፕዶሪያ ተሸነፉ
2-1 ቤንቬንቶን በሜዳቸው አሸነፉ
1-1 በሻምፒዮንስ ሊጉ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር አቻ ተለያዩ

የከዚህ ቀደም ግንኙነታቸው

ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታ ውጤታቸው ደግሞ የሚከተሉትን ይመስላሉ።

መጋቢት 5፣ 2017: ናፖሊ 3-2 ጁቬ (በኮፓ ኢታሊያ)
መጋቢት 2፣ 2017: ናፖሊ 1-1 ጁቬ
የካቲት  28፣ 2017: ጁቬ 3-1 ናፖሊ (በኮፓ ኢታልያ)
ጥቅምት 29፣ 2016: ጁቬ 2-1 ናፖሊ
የካቲት 13፣ 2016: ጁቬ 1-0 ናፖሊ
ናፖሊ

ቁጥራዊ መረጃዎች

 • ናፖሊና ጁቬንቱስ እ.ኤ.አ. ከ1993 ወዲህ ለ42 ጊዜያት ያህል ተገናኘተው ተጫውተዋል። በነዚያ ጨዋታዎችም ጁቬ 21 ጨዋታዎችን ድል ሲያደርግ ናፖሊ ደግሞ 11 ጨዋታዎችን አሸንፏል። በቀሪ አስር ጨዋታዎች ላይ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።
 • በሴሪ አው ወጥ አቋም ማሳየት የተሳነው ጁቬ ከ14
  ጨዋታዎች 11 አሸንፎ ሁለት ተሸንፎ አንድ አቻ ወቶ በ34
  ነጥብ ከመሪው ናፖሊ በ4 ነጥብ ርቆ ከተከታዩ ኢንተር በ2
  ነጥብ አንሶ በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 
 • ጁቬ በመጨረሻዎቹ 6 ጨዋታዎቹ 19
  ጎሎች ሲያስቆጥር የአጥቂው አስፈሪነት ያሳያል።
  የጉዳት ዜናዎች

በመጨረሻም

አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ በኔፕልስና በድፍን ጣልያን ብዙ ተመልካች ያለውን የማፊያ ቤተሰቦች ተከታታይ የቴሌቭዥን ደራማ ሁለት አዳዲስ ምዕራፎችን ከዛሬው ጨዋታ እኩል ያሳይ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ተጠባቂ የሴሪ አ ጨዋታ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ አራዝሟቸዋል። 

Advertisements