ድጋፍ / ካፍ አፍሪካን በአለም ዋንጫ ለሚወክሉ አምስቱ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳወቀ

1

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) በቀጣይ ሰኔ ወር በራሺያ ለሚጀመረው የ 2018 የአለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው ለሚሳተፉ አምስት ሀገራት ገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል፡፡

የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ህዳር 16 በሞሮኮ ራባት ባደረገው ስብሰባ አፍሪካን ወክለው በአለም ዋንጫው ላይ ለሚካፈሉ ቡድኖች ድጋፍ ለማድረግ በካፍ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ክዌሲ ኒያንታኪ የሚመራ ጊዚያዊ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት ካፍ ለነዚህ ተሳታፊ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው 500ሺ ዶላር ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን የገንዘብ ድጋፉም ለቡድኖቹ የቴክኒክ ቁጥጥር እና ለዝግጅት የሚውል ይሆናል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ልምምድ እቃዎች፣የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች፣አካል እንቅስቃሴ መለከያ መሳሪያዎችን ጨምሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል፡፡

የ 2018 የአለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ዛሬ አመሻሹ ላይ የሚታወቅ ሲሆን ለዚህም የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ካሉሺያ ቡዋሊያ፣እንዲሁም የአምስቱም ሀገራት እግርኳስ ፕሬዝዳንት በሞስኮ የሚገኙ ይሆናል፡፡

4.jpg

የተለያዩ ሽልማቶች እና ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው 6000 ሰው በሚይዘው ሞስኮ ላይ የሚገኘው ስቴት ክሪምሊን ፓላስ 32 ቱ ለአለም ዋንጫ ያለፉ ቡድኖች በአለም ዋንጫው የምድብ ተጋጣሚያቸውን የሚያውቁበት ቦታ ሲሆን ምሽት ላይ ስምንቱ ምድቦች ተለይተው ይታወቃሉ፡፡

ግብጽ፣ሞሮኮ፣ቱኒዚያ፣ናይጄሪያ እና ሴኔጋል አፍሪካን በመወከል በአለም ዋንጫው ላይ የሚሳተፉ ሀገራት እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

 

Advertisements