ሳምፓውሊ፡ ሮናልዶ በጣም ጎበዝ ነው፤ ምርጡ ግን መሲ ነው

የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ማን ነው? የሚለው አከራካሪ ርዕሰ ጉዳይ ዓለምን በሁለት እንደከፈለ ነው። ነገር ግን ጆርጌ ሳምፖውሊ ከሊዮኔል መሲ በላይ የተሻለ መምረጥ ከባድ እንደሆነ ያስባሉ።

የአርጄንቲናው አሰልጣኝ ጆርጌ ሳምፖሊ ባለፉት አስርት ዓመታት ከክርስቲያኖ ሮናልዶም በላይ መሲ “የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች” እንደሆነ አይጠራጠሩም። 

መሲ እና ሮናልዶ የ2017ን የባሎን ዶ’ሩ ሽልማት ለመውሰድ የሚደረገውን ፉክክር በቀዳሚነት በመምራት ላይ ቢገኙም የሪያል ማድሪዱ ፓርቱጋላዊ ኮከብ ግን ባለፈው ዓመት ማግኘት በቻላቸው የሻምፒዮንስ ሊግ እና የአውሮፓ ዋንጫዎች ምክኒያት የተሻለ የማሸንፍ ግምት ተሰጥቶታል። 

ነገር ግን ሳምፓውሊ ሮናልዶ “በጣም ጎበዝ” የሆነ ብቃት ያለው ተጫዋች መሆኑ ግልፅ እንደሆነ ቢያውቁም የትኛው ተጫዋች ምርጥ ነው ለሚለው ግን ቀዳሚ ምርጫቸው መሲ ነው።

ሳምፓውሊ ለድረገፅ የስፖርት ሚዲያው ኦምኒስፖርት እንደተናገሩት “ክርስቲያኖ በጣም ጎበዝ ተጫዋች ነው። ነገር ግን ባለፉት አስርት አመታት መሲ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች የነበረ ይመስለኛል፤ ይሰማኛልም። ነገር ግን ይህ የእኔ አስተያየት ነው። በግብ ብዛት፣ የግብ ዕድል በመፍጠር፣ በክህሎት፣ በአጨዋወት ዘዴው መሲ የተሻለ ነው። ነገር ግን አስተያየቱ የግሌ ብቻ ነው።” በማለት ነበር። 

ይሁን እንጂ ሳምፓውሊ ከሌሎች ተጫዋቾች ግን መሲና ሮናልዶ ተለይተው የሚቀማጡ እንደሆነም ገልፀዋል።

የቀሞው የሲቪያ አሰልጣኝ አክለው “ከእነሱ [መሲና ሮናልዶ] በኋላ ሌሎች እንደኔይማር ወይም ልዊስ ስዋሬዝ ያሉ ወይም እንደ [ኪሊያን] ምባፔ ወይም [ኦስማን] ዴምቤሌ ያሉ አንዳንድ ወጣት ተጫዋቾች አሉ። 

“ወደፊት ለቦታው ይፈለማሉ። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ መሲ እና ክርስቲያኑ መጫወታቸውን ቀጥለዋል። ሎሎቹ ደግሞ ለሶስተኝነት እና ለአራተኝነቱ ቦታ የሚፋለሙ ይሆናል።”

ሁልጊዜም በመሲ ብቃት ላይ የሚነሳ ብቸኛ ትችት ቢኖር ተጫዋቹ ከአርጄንቲና ጋር አንድ እንኳ አብይ ዋንጫ ማንሳት አለመቻሉ ነው። ይህ ደግሞ በአንዳንዶች ዘንድ ከታላቅ ተጫዋችነት ውጪ የሚያደረገው የመከራከሪያ ነጥብ ሆኖ ይነሳል። 

ነገር ግን ሳምፓውሊ በእዚህ አይስማሙም። አሰልጣኙ ይህን ሃሳብ አስመልክተው “ሁልጊዜም ምርጥ እንደሆኑ ይታሰባሉ ብዬ የማስባቸው ፔሌ፣ ማራዶናና አሁን ደግሞ መሲ ናቸው።

“ነገር ግን እሱ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ለመሆን በአውሮፓ አስርት ዓመታት ቆይቷል። በዚህ በተወሳሰበ የአውሮፓ እግርኳስ ላይም ከ500 በላይ ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

“በመሆኑም የዓለማችን ምርጥ ለመሆን የዓለም ዋንጫን ማግኘት አይኖርብህም።” ሲሉ የመሲን ኮከብነት ገልፀዋል፡

Advertisements