አርሰናል ከ ማንችስተር ዩናይትድ : የቅድመ ጨዋታ ትንታኔ

ጆሴ ሞውሪንሆ ከሜዳቸው ውጪ ትልልቆቹን ስድስቱን የሊጉ ቡድኖች ማሸነፍ ከቻሉና ቡድናቸው ዩናይትድ ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ አርሰናልን በሜዳው ድል ካደረገ ሶስት አመታት በተቆጠሩበት በዚህን ሰዓት ያለፉትን 12 ጨዋታዎች በሜዳው ያልተሸነፈውን የአርሰን ቬንገር ስብስብ ለመግጠም ወሳኝ አማካኙን ማቲችን ማሰለፉ አጠራጣሪ በሆነበት ሁኔታ ነገ ምሽት በፊት መስመር ላይ ላካዜቲን ማጣቱ ካለው ጠንካራ የፊት መስመር አንፃር ብዙም ችግር እንደማይፈጥርበት የሚጠበቀውን የመድፈኞቹን ስብስብ ይገጥማል። የኢትዮአዲሱ ሚኪያስ በቀለም የጨዋታው ውጤት ለሁለቱም ቡድኖች የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ሆኖ መቀጠል ወሳኝ ሚና ያለውን የምሽቱን ተጠባቂ ትንቅንቅ የቅድመ ጨዋታ ወሳኝ ነጥቦች በሚከተለው መልኩ ይዞ ተገኝቷል።


ጨዋታው የሚደረግበት ሰአት : ምሽት 2:30

ቦታ : ኢምሬትስ

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤት : አርሰናል 2-0 ማንችስተር ዩናይትድ

ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት የሚያገኝበት የቴሌቪዥን ጣቢያ : ሱፐር ስፖርት፣ ቢቲ ስፖርት 1 (በመላው እንግሊዝ) እና ቤን ስፖርት (ለመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ)

የጨዋታው ዳኛ : አንድሬ ማሪነር

በዘንድሮው የውድድር ዘመን የጨዋታው ዳኛ አቋም : ጨዋታ 10፣ ቢጫ 26፣ ቀይ 1፣ በየጨዋታው 2.80 ካርዶች መዘዋል 

                               አርሰናል

ተጠባቂ አሰላለፍ : ቼክ፣ ኮሽሊኒ፣ ሙስጣፊ፣ ሞንሪያል፣ ራምሴይ፣ ዣካ፣ ቤለሪን፣ ኮላስንያሊክ፣ ኦዚል፣ ጂሩድ፣ ሳንቼዝ

ተቀያሪዎች : ማቺ፣ ኦስፒና፣ ሊቪ፣ ድቡቺ፣ ሚትላንድ- ናይልስ፣ ኮክለን፣ ኤልኒኒ፣ ዊሊሼር፣ ዋልኮት፣ ኢዎቢ፣ ኔልሰን፣ አክፖም፣ ሜርትሳከር

በጨዋታው ላይ መሰለፋቸው የሚያጠራጥር : የለም

ጉዳት : ላካዜቲ (ብሽሽት)፣ ካዞርላ (ቋንጃ)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : አአሽድድድ

ስነምግባር : ቢጫ 19፣ ቀይ 0

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ላካዜቲ 7

የቬንገር አስተያየት : “ማንችስተር ዩናይትድ ጠንካራ ቡድን እና እኛን የሚፈትን ችግር እንደሚሆን እጠብቃለሁ። መከላከል ብቻ ሳይሆን በደንብ ያጠቁናልም።    

“… ዩናይትድ ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ቡድን ሲሆን እኛም ጥሩ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። ስለዚህ ጥሩ ጨዋታ የሚሆን ይመስላል።”                              

                     ማንችስተር ዩናይትድ

ተጠባቂ አሰላለፍ : ዴይኻ፣ ሮሆ፣ ስሞሊንግ፣ ያንግ፣ ቫሌንሲያ፣ ፖግባ፣ ማቲች፣ ረሽፎርድ፣ ማታ፣ ማርሻል፣ ሉካኩ

ተቀያሪዎች : ፔሬራ፣ ሮሜሮ፣ ቱአንዜቤ፣ ሊንድሎፍ፣ ሊንጋርድ፣ ማክቶምናይ፣ ሚሼል፣ ዳርሚያን፣ ብሊንድ፣ ሾው፣ ኢብራሞቪች፣ ሄሬራ፣ ማኪቴሪያን

በጨዋታው ላይ መሰለፋቸው የሚያጠራጥር : ካሪክ፣ ማቲች (ሁለቱም ለጨዋታው ብቁ ሆኖ ከመገኘት ጋር በተያያዘ

ጉዳት : ቤሊ (ብሽሽት)፣ ጆንስ (ዳሌ)፣ ፌላኒ (ጉልበት)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : ሽድሽድድድ

ስነምግባር : ቢጫ 19፣ ቀይ 0

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ሉካኩ 8

የጆሴ ሞውሪንሆ አስተያየት : “… ትልልቅ ጨዋታዎችን አስታውሳለሁ። ወደእንግሊዝ ከመምጣቴ በፊት ለብዙ አመታት ሁኔታው ማንችስተር ከ አርሰናል ከሆነ የዋንጫ ፍልሚያ ነበር።” 

Advertisements