ስለሴካፋ ውድድሮች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች

በዓለም አቀፉ የእግርኳስ አመራር አካል (ፊፋ) ተባባሪነት የሚካሄደውና ከአፍሪካ ውድድሮች ሁሉ በምስረታው አንጋፋ የሆነው የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ሃጋራት እግርኳስ ማህበራት (ሴካፋ) ውድድሮች አንዱ የሆነው የሴካፋ ሲኒየርስ ቻሌንጅ ካፕ በኬንያ አዘጋጅነት ከዛሬ እሁድ አንስቶ መካሄድ ይጀምራል። ኢትዮአዲስስፖርትም ኢትዮጵያም ጭምር ስለምትሳተፍበት አመታዊ ውድድር ሊያውቋቸው ይገባሉ ያለቻቸውን ጉዳዮች እንደሚከተለው አሰናድታለች።

የውድድሩ ምስረታ ምን ይመስላል?

ሴካፋ እ.ኤ.አ. 1927 ብሪታንያውያኑ ወንድማማቾች ባለቤትነት በሚተዳደረውና መሰረቱን ናይሮቢ፣ ኬንያ ላይ ባደርገው ጎሳጅ በተሰኘ የሳሙና ፋብሪካ ስፖንሰርነት ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የተመሰረተ ውድድር ነው። 

ውድድሩ “ኢስት አፍሪካን ቻሌንጅ ካፕ” ወደሚል ስያሜ እስከተቀየረበት እስከ60ዎቹ አጋማሽ ድረስ “ጎሳጅ ካፕ” በሚል ስያሜ ለ37 ጊዜያት ያህል ሲካሄድም ቆይቷል። “ኢስት አፍሪካ ሲኒየርስ ቻሌንጅ ካፕ” በሚለው ስያሜም እስከ1971 ድረስ ለሰባት ጊዜያት ያህል ውድድር ተካሂዶ በመቆየት በ1973 አሁን የየያዘውን ሴካፋ (የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ የእግርኳስ ማህበራት ተወካዮች) የሚል ስያሜ በመያዝ እስካሁን እየተከሄደ ይገኛል።

የሴካፋ ሲኒየርስ ቻሌንጅ ካፕ ውድድር እ.ኤ.ኤ.በተለያዩ ጊዜያት አሁን በሳውዲ አረቢያ በሙስና ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት ሼህ አሊ አላሙድን ስም እና ከምስራቅ አፍሪካው የቢራ አምራች ኩባንያው ተስከር ጋር የስፖንሰር ስምምነቶችን በማድረግ ለሁለት ጊዜያት ያህል የስያሜ ለውጦችንም አድርጓል።

ሴካፋ ምን ዓይነት ውድድሮች አሉት?

ዋና መስሪያ ቤቱን በኬንያዋ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ ያደረገው ሴካፋ በስሩ ከታች የተዘረዘሩትን ስድስት የውድድር ዓይነቶችን ያካሂዳል።

  •  የሴካፋ አባል ሃገራት የሚሳተፉበት ሴካፋ ሲነየርስ ቻሌንጅ ዋንጫ
  • የሴካፋ አባል ሃገራት ክለቦች የሚሳተፉበት የሴካፋ ክለብ ዋንጫ 
  • የተመረጡ የሴካፋ አባል ሃገራት ክለቦች የሚሳተፉበት ሴካፋ ናይል ቤዚን ዋንጫ
  • የሴካፋ አባል ሃገራት ከ17 ዓመት በታች ቡድኖች ተሳታፊ የሚሆኑበት የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮን ሺፕ 
  • የሴካፋ አባል ሃገራት ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ተሳታፊ የሚሆኑበት ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮንሺፕ

የውድድሩ አባል ሃገራት እነማን ናቸው?

ሴካፋ በየዓመቱ በሚያደርጋቸው ውድድሮች በተጋባዥነት ከሚያሳትፋቸው ሃገራት በተጨማሪ ከታች የተዘረዘሩት 12 መደበኛ አባል ሃገራት አሉት።

የሴካፋ አባል ሃገራት

የዚህ ዓመት የሴካፋ ሲንየርስ ቻሌጅ ካፕ ውድድር የት እና መቹ ይካሄዳል?

ከሴካፋ ስድስት ውድድሮች መካከል ዋነኛ የሆነውና ኡጋንዳ ለ13 ጊዜያት ያህል በማሸነፍ ቀዳሚ የሆነችበት የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ካፕ ከደቡባዊ አፍሪካ ዚምባብዌን እንዲሁም ከሰሜን አፍሪካ ሊባያን በእንግድነት በመጋበዝ ከዛሬ ህዳር 24፣ 2010 እስከ ታህሳስ 8፣ 2010 ዓ.ም ድረስ አስር ሃገራት ማለትም አዘጋጇን ኬንያን ጨምሮ ያለፈው ዓመት አሸናፊዋ ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ብሩንዲን፣ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳንና ዛንዚባር በሁለት ምድብ በመክፈል ይከናወናል።

ምድብ ሀ ምድብ ለ
ኬንያ ኡጋንዳ
ሩዋንዳ ዚምባብዌ
ሊቢያ ቡሩንዲ
ታንዛኒያ ኢትዮጵያ
ዛንዚባር ደ.ሱዳን

የጨዋታ መርሃግብሮቹ የሚከተሉት ናቸው።

ጨዋታውን እንዴት መመልከት ይችላሉ?

እ.ኤ.አ. ከ2009 አንስቶ የዚህን ውድድር የቴሌቭዥን ስርጭት መብቱት የደቡብ አፍሪካው ሱፐርሱፖርት በብቸኝናት መግዛቱን ተከትሎ ጨዋታዎችን በሱፐርስፖርት ቻናሎች በቀጥታ ማመልከት ይቻላል።

Advertisements