“ ቶትንሀም በሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ደረጃ አይገኝም̋” – ማውሪሲዮ ፖቾቲንሆ

የቶትንሀሙ ሆትስፐርስ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቾቲሆ የለንደኑ ክለብ  ውጤት አልባ ጉዞን ተከትሎ እየደረሱ ያሉ ወቀሳዎች እንዳላስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡ አርጀንቲናዊው ቆፍጣና አለቃ ክለባቸቸው ባለፉት 4 የሊግ ጨዋታዎች ላይ ሙሉ 3 ነጥቦች አለማስመዝገቡን ተከትሎ ከወዲሁ ከመሪው ማንችስተር ሲቲ በ18 ነጥቦች ቢርቅም እየመጡ ያሉ ትችቶች ተገቢ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰዎች የሚሰጧቸው የትችት አስተያየቶች እኔንም ሆነ የክለቡን ተጫዋቾች እንዲሁም የአሰልጣኞች ስታፍ አባላትን ይበልጥ እንድንሰራ በር ይከፍቱልናል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ትችቶች ተገቢ አይደሉም በአሁኑ ሰዓት ጥሩ የማይባል የውድድር ዘመን እያሳለፍን ባንገኝም ባለፉት ሶስት አመታት በሊጉ ተፎካካሪ ነበርን ፡፡

ሆኖም ሰዎች ሊረዱ የሚገባቸው ነገር እኛ ባርሴሎናን ወይም ሪያል ማድሪድ አይደለንም ለተከታታይ ጊዜያት እያሸነፍን የምንዘልቀው በእንርሱ ደረጃ ለመሆን ብዙ ይቀረናል፡፡ በማለት በቅርቡ በክለቡ ዙሪያ እየመጡ ያሉ ትችቶችን አስተባብለዋል፡፡

ቶትንሀም ሆትስፐርስ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ቢርቀውም በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን ከአምናው የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድም ተሸሎ ምድቡን በበላይነት እየመራ ይገኛል፡፡

Advertisements