የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ 27 ግቦች ከመረብ ላይ አርፈዋል። ከእነዚህ መከካከል ደግሞ ስድስቱ የተቆጠሩት ሊቨርፑል ብራይተንን 5ለ1 ማሸነፍ በቻለበት የአሜክስ ስታዲየም ጨዋታ ላይ ነበር። አራቱ ግቦች ደግሞ አርሰናል ካደረጋቸው 33 ሙከራዎች 15 ዒላማቸውን የጠበቁ መከራዎችን አድርጎ ነገር ግን በማንችስተር ዩናይትድ 3ለ1 የተሸነፈበት በኢመሬትስ ስታዲየም የተደረገው ጨዋታ ላይ የተቆጠሩ ነበሩ።

ሌሎቹ ደግሞ ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ ኒውካሰልን 3ለ1 በረታበት፣ ማንችስተር ሲቲ ዌስት ሃምን በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት 2ለ1 በማሸነፍ 13ኛ የፕሪሚየር ሊጉ ድሉን ባስመዘገበበት፣  እንዲሁም ስቶክ ስዋንሲን 2ለ1 በመርታት ሶስት ወሳኝ ነጥብ በገኘበት ጨዋታ ላይ የተመዘገቡ ግቦች ነበሩ።

በእነዚህ ጨዋታዎችም ጎል ድረገፅ ለክለባቸው ውጤታማነት የግላቸውን ከፍተኛ ድርሻ የተወጡ እና በሳምንቱ ምርጥ 11 የቡድን ስብስብ ውስጥ መግባት ችለዋል ብሎ የዘረዘራቸውን ተጫዋቾች እንደሚከተለው ተመልክተናቸዋል።


ዴቪድ ደ ኽያ | ማ.ዩናይትድ

David de Gea, Manchester United

ግብ ጠባቂው ከአርሰናል ጋር በተደረገው ጨዋታ የዓለማችን ምርጡ ግብ ጠባቂ እንደነበር ማሳየት ችሏል፤ ያከሸፋቸው 14 የግብ ሙከራዎችም ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት 14 ዓመታት በፕሪሚየር ሊጉ በጥምር ብዙ ጨዋታዎችን አሸናፊ መሆን የቻለ ክለብ እንዲሆን ያስቻሉ ነበሩ።


ካይል ዎከር | ማን ሲቲ


Kyle Walker Premier League Team of the Week

የቀኝ መስመር ተከላካዩ ከቡድን አጋሩ ፋቢያን ደልፍ ጋር በተስተካካይ አምስት ስኬታማ ኳስ የማጨናገፍ ሸርተቴዎችን በማድረግ ቡድኑ በአንድ የግብ ልዩነት ዌስት ሃምን እንዲያሸንፍ ጠንካራ የሆነ ሚናውን ማሳየት ችሏል።


ርያን ሻውክሩዝ | ስቶክ ሲቲ


Ryan Shawcross Premier League Team of the Week

ሻው ክሩዝ ቡድኑን 12 ግብ  የማንፃት ስራ እንዲሰራ እና ስቶክ ስዋንሲ ሲቲን 2ለ1 እንዲያሸንፍ ያስቻለ ቁልፉ ሰው ነበር።


አሽሊ ዊሊያምስ | ኤቨርተን


Ashley Williams Everton

ኤቨርተን በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት ያስቻለውን ሁለተኛ ድል ኸደርስፊልድን 2ለ0 ሲያሸንፍ የቶፊሶቹ ተከላካይ 13 የግብ ማምከን ስራ ሰርቷል።


ሪያን በርትራንድ | ሳውዛምፕተን


Ryan Bertrand Premier League Team of the Week

ምንም እንኳ ቅዱሳኑ ከቦርንማውዝ ጋር 1ለ1 በሆነ ውጤት ቢለያዩም በርትራንድ ግን በጨዋታ ከየትኛውም ተጫዋች በላይ ከፍተኛ የሆነውን ሶስት የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችሏል።


ኬቨን ደ ብሩይኔ | ማን ሲቲ


Kevin De Bruyne Premier League Team of the Week

ቤልጂየማዊው ተጫዋች ዌስት ሃምን እንዲያሸንፉ ያስቸለቻቸውን ግብ ዴቪድ ሲልቫ እንዲያስቆጥር የግብ ዕድል በማመቻቸት አሁንም የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን ማረጋገጡን ቀጥሎበታል። ደ ብሩይኔ ከየትኛውም የሲቲ ተጫዋች በላቀም በርካታ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ያቀበለ ሲሆን፣ ማቀበል ከቻላቸው 114 ኳሶች ውስጥም 93ቱ በተቃራኒ ቡድን የሜዳ አጋማሽ ክልል ውስጥ ያቀበላቸው ነበሩ።


ዳቪድ ሲልቫ | ማን ሲቲ


David Silva Premier League Team of the Week

የሲቲን የድል ግብ ያስቆጠረው ሲልቫ ክለቡ በስምንት ነጥቦች ብልጫ በደረጃው አናት ላይ እንዲቀጥል ከሁሉም የቡድን አጋሮቹ በላይ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችሏል።


ፊሊፔ ኮቲንሆ | ሊቨርፑል


Philippe Coutinho Premier League Team of the Week

ብራዚላዊው ተጫዋች ሊቫርፑል ብራይተንን 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ በቻለበት ጨዋታ አንድ ግብ በማስቆጠር፣ አንድ ግብ ደግሞ ብራይተኖች በራሳቸው ግብ ላይ እንዲያስቆጠሩ በማድረግ እንዲሁም ሁለት ግቦች እንዲቆጠሩ አመቻችቶ በማቀበል የጨዋታው ኮከብ ነበር።


ጄሴ ሊንጋርድ | ማን ዩናይትድ


Jesse Lingard Premier League Team of the Week

ቀያይ ሰይጣኖቹ አርሰናልን በኤመራትስ የግብ ብልጫ እንዲወስዱ በማደረጉ በኩል ሊንጋርድ በማጥቃቱ እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ሚና ነበረው። ክለቡ ካደረጋቸው አራት ዒላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች መካከል ሶስቱን ያደረገውም እሱ ነበር፤ ሁለቱን ደግሞ መረብ ላይ ማሳረፍ  ችሏል።


ሮቤርቶ ፊርሚኖ | ሊቨርፑል


Roberto Firmino Liverpool Brighton

ብራዚላዊው ክለቡ ከብራይተን ጋር ባደረገው ጨዋታ ሁለት ዒላማቸውን የጠበቁ ኳሶችን ወደግብ የመታ ሲሆን፣ ሁለቱም ደግሞ መረብ ላይ በማረፍ ቀዮቹን በደረጃ ሰንጠረዡ ወደአራተኛ ከፍ እንዲሉ አስችለዋል።


ኤዲን ሃዛርድ | ቼልሲ


Eden Hazard Chelsea Newcastle United 02122017

ሃዛርድ ቅዳሜ ዕለት ያደረጋቸው ዘጠኝ ዒላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎች የኒውካሰል ተጫዋቾች በሙሉ ካደረጉት ሙከራ የሚበልጥ ነበር። ከእነዚህ ሙከራዎቹም ሁለቱ ውጤታማ ሆነው ሰማያዊዎቹ ጨዋታውን 3ለ1 እንዲያሸንፉ አድርገዋል።

Advertisements