ኤፍ ኤ ካፕ / የእንግሊዝ የ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር ተጋጣሚዎች ታወቁ

አንጋፋው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሶስተኛ ዙር ተጋጣሚዎች የእጣ ድልድል ሰኞ ምሽት ይፋ ሲደረግ ታላላቆቹ ቡድኖች እርስ በርስ ተገናኝተዋል።

ምሽት ላይ ይፋ በሆነው የ 2017/2018 የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሶስተኛ ዙር ድልድል የደርቢ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ተጠባቂ ፍልሚያዎችን አገናኝቷል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባላንጣዎቹ መቀመጫቸውን ሊቨርፑል ያደረጉት የየርገን ክሎፑ ሊቨርፑል እና የሳም አላርዳይሱ ኤቨርተን በሶስተኛው ዙር ከሚጠበቁ ጨዋታዎች ውስጥ ዋነኛው ነው።

ሁለቱ ቡድኖች በኤፍ ኤ ካፕ በሶስተኛው ዙር ሲገናኙ ከ 1932 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል።ኤቨርተን ዘንድሮ የተጠበቀውን ያህል ጠንካራ ሆኖ ባይቀርብም አሰልጣኝ መቀየሩ እንዲሁም የከተማውን ቡድን ማግኘቱ ቀላል ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም።

ሌላው በፕሪምየርሊግ የሚሳተፉት ክርስቲያል ፓላስ እና ብራይተን የሚገናኙ ሲሆን ፣በሰሜን ምስራቅ ደርቢ ደግሞ ሰንደርላንድ ከ ጎረቤቱ ሚድልስቦሮ ይጫወታል።

የፕሪምየርሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሀድ በርንሌን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ሌላው የፕሪምየርሊግ ተሳታፊን እርስ በርስ ያገናኘ ጨዋታ ነው።

አርሰናል ደግሞ ከሜዳው ውጪ ተጎዞ የቀድሞ ስመ ገናና የነበረውን ኖቲንግሀም ፎረስትን ሲገጥም የጆሴ ሞሪንሆው ዩናይትድ ደግሞ ደርቢን በሜዳው ያስተናግዳል።

ሙሉ ድልድሉን ይመልከቱ

ኢፕስዊች ከ ሼፊልድ ዩናይትድ

ዋትፎርድ ከ ብሪስቶል ሲቲ

በርሚንግሀም ከ በርተን

ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን

ብራይተን ከ ፓላስ

አስቶንቪላ ከ ዎርኪንግ/ፒተርብሮ

ቦርንማውዝ ከ ኤኤ ፍሲ ፊልድ/ዊጋን

ኮቨንትሪ ከ ስቶክ

ኒውፖርት ከ ሊድስ

ቦልተን ከ ኸደርስፊልድ

ፓርትቬል/ዮቪል ከ ብራድፎርድ

ኖቲንግሀም ፎረስት ከ አርሰናል

ብሬንትፎርድ ከ ኖንትስ ካንትሪ

ኪው ፒ አር ከ ኤም ኬ ዶንስ

ማን ዩናይትድ ከ ደርቢ

ፎረስት ግሪን/ኤግዚተር ከ ዌስትብሮም

ዶንካስተር ከ ስሎው ታውን/ሮቻዴል

ቶተንሀም ከ ዊምብልደን

ሚድልስቦሮ ከ ሰንደርላንድ

ፍሊትውድ/ሂርፎርድ ከ ሌሲስተር

ብላክበርን/ክሪው ከ ሀል ሲቲ

ካርዲፍ ከ ማንስፊልድ

ማን ሲቱ ከ በርንሌ

ሽርውስበሪ ከ ዌስትሀም

ዎልቭስ ከ ስዋንሲ

ስቲቨኔጅ ከ ሬዲንግ

ኒውካስትል ከ ሉተን

ሚልዎል ከ ባርንስሌ

ፉልሀም ከ ሳውዝሀምፕተን

ዋይኮምብ ከ ፕሪስተን

ኖርዊች ከ ቼልሲ

ጂሊንግሀም/ካርልስሌ ከ ሼፍልድ ዌ የሚገናኙ ሲሆን ጨዋታዎቹ በፈረንጆቹ አዲስ አመት ከጥር 5 እስከ ጥር 8 ድረስ የሚካሄዱ ይሆናል።

Advertisements