የማክሰኞ ምሽት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ዳሰሳ

ዛሬ ምሽት የሚደረጉ ከፊል የሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታዎች በቀደሙ ጨዋታዎች ቀጣዩን 16 ክለቦች ተሳታፊነታቸውን ካረጋገጡ ክለቦች በተጨማሪ ዛሬ የሚያረጋግጡ ክለቦች እንዲሁም በተጨማሪ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ያልቻሉ ነገር ግን በሶስተኛ ደረጃ የሚያጠናቅቁ 32 ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑበትን የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ውድድርን በጊዜ የሚቀላቀሉበት ይሆናል። ተከታዩ ፅሁፍም ዛሬ ምሽት በተመሳሳይ ምሽት 4፡45 ከሚደረጉ ስምንት ጨዋታዎች መካከል ለማለፍ የሚደረግ ትንቅንቅ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠበቁ አበይት ጨዋታዎችን እና ዝቅተኛ ግምት የተሳጣቸውን ሌሎቹን ጨዋታዎች ያስቃኝዎታል።

ቼልሲ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ (4፡45′)

ቼልሲ ባለፈው መስከረም ወር የዚህን ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታ ሲያሸንፍ በምድቡ ላይ የሚፎካከሩትን በሙሉ ቀድሞ እንደሚገኝ አስቀድሞ ያመላከተ ነበር።

ነገር ግን የአንቶኒዮ ኮንቴው ቡድን በሁለት ወር ከግማሽ ጊዜ ውስጥ በፍጥነት በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ጭምር በርካታ የውጤት መንሸራተት ተግዳሮቶች ገጥመውታል። በተለይም በዚህ ውድድር ላይ ከሮማ ጋር ለሁለት ጊዜያት ያህል ከባድ ትግል ገጥሞት ነበር።

ለሰማያዊዎቹ መልካም ዜና ቢኖር ግን ይህ ሁሉ ሆኖ እንኳ ከወዲሁ 16ቱን የጥሎ ማለፍ ዙር መቀላቀል መቻሉ ነው። በመሆኑም የስታንፎርድብሪጁ ክለብ ይህን ጨዋታ የሚያዳርገው የምድቡ ቀዳሚ ሆኖ ለመጨረስ ብቻ ይሆናል።

አትሌቲኮም ወደጥሎማሉፉ ዙር የማለፍ ዕድል ለማግኘት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በተደጋጋሚ የገጠመውን ቼልሲን የግድ ማሸነፍ ይኖርበታል።

የዲያጎ ሲሞኒው ቡድን በስታንፎርድ ብሪጅ የሚያደረገውን ይህን ጨዋታ የግድ ማሸነፍ ብቻም ሳይሆን በጣሊያኗ ዋና ከተማ ሮማን የሚገጥመው ካራባግ ጨዋታውን እንዲያሸንፍለት ፀሎት ማድረግ ይጠበቅበታል።

አትሌቲኮ ባለፉት ሳምንታት ካደረጋቸው ስድስት ጫዋታዎች አምስቱን በመርታት እና ከማድሪድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ብቻ በአቻ ውጤት በማጠናቀቁ ለዚህ ጨዋታ አስፈሪ አቋም ይዞ እንደሚገባ ይጠበቃል።

ሌላው ለአትሌቲኮ ይህ ጨዋታ የተለየ ጥቅም ሊሰጠው የሚችልበት ነገር ቢኖር ቼልሲ በፕሪሚየር ሊጉ የፊታችን ቅዳሜ በምዕራብ ለንደን ደርቢ ከዌስት ሃም ጋር ከባድ ጨዋታ የሚጠብቀው በመሆኑ ብዙም ግምት ለማይሰጠው ለዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ዋና ዋና ተጫዋቾቹን ሊያሳርፍም የሚችል መሆኑ ነው።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሲኤስኬኤ ሞስኮ (4፡45′)

በይፋ ዩናይትድ 16 ውስጥ ማግባቱ እርግጥ ባይሆንም ወደቀጣዩ ዙር እንዳያልፍ ሊያደረገው የሚችለው ነገር ቢኖር ግን የግድ በሰባት የግብ ልዩነት መሸንፈነፍ ብቻ ነው።

ይህ በኦልትራፎርድ የሚደረገው ጨዋታ ደግሞ በዚህ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ተብሎ አይጠበቀም። ከዚህ ይልቅ ጨዋታው ለዩናይትድ የምድቡ አናት ላይ ሆኖ ለመጨረስ የሚደርግ ፍልሚያ ሲሆን። በአንፃሩ ለተጋጣሚ ለሲኤስኬ ሞስኮ ግን በዚህ ምድብ ከባሰል ጋር በእኩል ነጥብ ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ዩናይትድን ለማሸነፍ የግድ ፍልሚያ ማድረግ የሚጠበቅበት መሆኑ ጥርጣሬ ውስጥ አይገባም።

በሌላው የዚህ ምድብ ጨዋታ ባሰል በቤኔፊካ የሚሸነፍ ከሆነ ሲኤስኬዎች ማንችስተር ዩናይትድን የግድ ማሸንፈ ሳይጠበቅባቸው ይልቁንስ ሁለቱም ተያይዘው ማለፍ የሚችሉበት ዕድል የሚያገኙ ይሆናል።

ምናልባት ግን አቻ የሚለያዩ ከሆነ ያለግብ እንዲጠናቀቅ ማደረግ ይጠበቅባቸውል። ዩናይትድ ግብ የሚያስቆጥር ከሆነ ግን ሲኤስኬኤዎች ከውድድሩ ውጪ ሊወጡ የሚችሉበት ሁኔታም አለ። 

ሆዜ ሞሪንሆ በዚህ ጨዋታ ላይ የተወሰኑ ለውጦችን እንደሚያደርጉ ነገር ግን ፖል ፖግባ በሊጉ ቅጣት ያለበት በመሆኑ በዚህ ጨዋታ ላይ የመኃል ሜዳውን ሚና እንደሚወስድ ሲገልፁ፣ ሲኤስኬዎች ደግሞ በቅጣት ምክኒያት ቢንራስ ናቾንና ፖንተስ ወርንብሉምን በዚህ ጨዋታ ላይ አገልግሎታቸውን አያገኙም።

ሴልቲክ ከ አንደርሌክት (1፡45′)

ሁለቱም ክለቦች ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ አይችሉም። ነገር ግን ይህን ጨዋታ ትልቅ የሚያደረገው አንድ ምክኒያት አለ። ይኸውም ይህን ጨዋታ የሚያሸንፍ ቡድን ምድቡን በሶሰተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎ ማግኘት የሚችል መሆኑ ነው። 

በተለይም በመጀመሪያው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በብራሰልስ 3ለ0 ማሸነፍ የቻለው ሴልቲክ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመትም ከአውሮፓ ውድድር ያለመውጣት የተሻለ ዕድል አለው።

አንደርሌክቶችስ ይህን ጨዋታ ከሶስት ግቦች በላይ በማሸነፍ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችሉ ይሆን? የሚሆን ነገር ባይመስልም በእግርኳስ ጨዋታዎች ላይ የተከሰቱ የከዚህ ቀደም ውጤቶችን ለተመለከተ ግን የሄን ባንሃዘብሮኩ ቡድን አብቅቶለታል ብሎ ድምድሜ ላይ መድረስ አስቸጋሪ ነገር ነው።

ሌሎች ወሳኝ የምሽቱ ጨዋታዎች

ሮማ፣ ባሰል እና ጁቬንቱስ የሚያደርጓቸውን ጨዋታዎች ካሸነፉ ወደቀጣዩ 16ቱ የጥሎ ማለፍ ዙር ማለፍ የሚችሉ ይሆናል፤ በቀላሉ እንደሚያልፉም ይጠበቃል። ምክኒያቱም የሶስቱም ተጋጣሚዎቻቸው የሆኑት እንደቅደም ተከተላቸው ካራባግ፣ ቤኔፊካና ኦሎምፒያኮስ አስቀድመው አለማለፋቸውን ያረጋገጡት እና የሚያደረጉት ጨዋታ ፋይዳ የሌለው ነው።

ጁቬዎች ማሸነፍ ወደቀጣዩ ዙር እንደሚያሳልፋቸው ቢያውቁም፣ ከሜዳው ውጪ ባርሴሎናን የሚገጥመው ስፖርቲንግ ሊዝበን በማንኛውም ውጤት ሽንፈት ከገጠመው ደግሞ በቀላሉ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችላሉ።

ቤኔፊካን የሚፈገጥመው ባሰል ግን ሲኤስኬኤ በማንችስተር እንዲሸነፍ ተስፋ ከማድረግ በተጨማሪ ቢችል ጨዋታውን ማሸነፍ ካልሆነም በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል። ይሁን እንጂ በዚህ ምድብ ያዳረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ ሽንፈት የደረሰበት እና በውድድሩ ላይ አንድ ግብ ብቻ አስቆጥሮ 12 የግብ ዕዳዎችን የተሸከመው እና መጥፎ ብቃት ያሳየው ቤኔፊካ ባሰልን ያሸንፋል ተብሎ አይጠበቅም።

ከላይ ከተነሱት ጨዋታዎች ሁሉ ለየት ያለ ጨዋታ የሚሆነው ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ የሚያደረጉት ጨዋታ ነው። ሁለቱም ክለቦች ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም የምድቡ የበላይ የሚሆነው ክለብ ግን እስካሁን አልተለየም። ይህን በምሽቱ ጨዋታ ለመለየት ግን በአምስት የግብ ክፍያ እና በ12 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የጀርመኑ ክለብ ከምድቡ ቀዳሚ ሆኖ ለመቀመጥ 15 ነጥብና 23 ንፁህ የግብ ክፍያ ያለውን የፈረንሳዩን ክለብ ይሆናል ተብሎ በማይታሰብ ሁኔታ በ18 የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ምድብ ኤ

# ክለብ ነጥብ
1 12
2 9
3 9
4 0

ምድብ ቢ

# ክለብ ነጥብ
1 15
2 12
3 3
4 0

ምድብ ሲ

# ክለብ ነጥብ
1 Previous rank: 2 10
2 Previous rank: 1 8
3 6
4 2

ምድብ ዲ

# ክለብ ነጥብ
1 11
2 8
3 7
4 1

Advertisements