የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዕጩዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እግርኳስ አመራርነት ሚናን ለቀጣዮቹ ዘመና በፕሬዝድንትነት እና በስራ አስፈፃሚነት ለመምራት ለሚደረገው የምርጫ ፉክክር ተወዳዳሪ ናቸው ያላቸውን 21 የዕጩዎች ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ ሰኞ ህዳር 25፣ 2010 ዓ.ም አደረግኩት ባለው ስብሰባ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድርን እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዩ አቶ ጁነዲን ባሻህ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዩ አቶ ተካ አስፋው፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዩ አቶ ኢሳያስ ጂራ፣ የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዩ አቶ ዳግም መላሼ ለፕሬዝዳንነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ናቸው ብሉ ባወጣው ዝርዝር ላይ አስፍሯቸዋል።

በተጨማሪም ለስራፈፃሚ ኮሚቴነት የሚወዳደሩ ናቸው ያላቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳዳር እግርኳስ ፌዴሬሽን ሶስት ተወካዮች፣ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ሶስት ተወካዮች፣ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ሁለት ተወካዮች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድርን እግርኳስ ፌዴሬሽን፣ ከሃረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን፣ ከኢትዮጵያ ሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን፣ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን እያንዳድንዳቸው አንድ አንድ ተወካዮችን በድምሩ 16 ተወካዮችን ስም ዝርርዝር በይፋዊ የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ማህበራዊ ገፅ ላይ ለጥፏል።

ኮሚቴው ይፋ ያደረገው መግለጫ ምክኒያቱን ባይገለፅም ተወዳዳሪነታቸው ያልፀደቁ ተብለው የሀረሪ ብሔራዉ ክልላዊ መንግስት እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካይ የሆኑትን አቶ ሙራድ አብዲን እና የኢትዮጵያ ዳኞች ማህበር ተወካዩን አቶ ልዑል ሰገድ በጋሻው ኮሚቴው ይፋ ባደረገው ዝርዝሩ ላይ ስማቸው ሰፍሯል።

አስመራጭ ኮሚቴው ተወዳዳሪነታቸው ያልፀደቀ ያላቸውን   ተወካዮች ጨምሮ ለፕሬዝዳንትና ለስራአስፈፃሚነት ኮሚቴ ይወዳደራሉ ብሎ ስማቸውን ይፋ ካደረጋቸው 23 ተወካዮች መካከል ብቸኛዋ ሴት ተወካይ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እግርኳስ ፌዴሬሽን ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴነት እንዲወዳደሩ የወከላቸው ወ/ሮ ሶፊ አልማሙን ብቻ ናቸው።

ሙሉ ዝርዝሩን ከታች ይመልከቱ።

Advertisements