ማርክ ክላተንበርግ ለምን ከፕሪምየርሊጉ የዳኝነት ስራቸው አቆሙ?

8

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በመምራት ይታወቁ የነበሩት ማርክ ክላተንበርግ ከ 2017/2018 ጀምሮ የፕሪምየርሊጉ የዳኝነት ስራቸውን አቁመው ወደ ሳውዲአረቢያ አቅንተዋል፡፡ክላተንበርግ በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ስራቸውን ለማቆም ያስገደዳቸው ምክንያት ከአንድ አሰልጣኝ የቀረበባቸው ትችት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡የቀድሞው ዳኛ ባለፈው አመት የቼልሲ እና የቶተንሀም ጨዋታ ላይም ሶስት የስፐርስ ተጫዋቾችን ከሜዳ በቀይ መውጣት ቢገባቸውም ሆን ብለው እንዳለፏቸው ተናግረዋል፡፡

በሳውዲአረቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ሀላፊ ሆነው እየሰሩ ያሉት ማርክ ክላተንበርግ በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ለረጅም አመታት በመስራት ይታወቃሉ፡፡እኝህ በዱርሀም የተወለዱት ዳኛ ገና 42 አመታቸው ቢሆንም የፕሪምየርሊጉን ዳኝነት ስራቸውን አቁመው ወደ ሳውዲአረቢያ አምርተዋል፡፡

ክላተንበርግ በተለይ 2016 ታላላቅ ጨዋታዎችን በመምራት ቅድሚያውን ይዘው እንደነበር ይታወሳል፡፡በጊዜው የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ እንዲሁም የ2016 የአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ጭምር በመምራት በፊፋ በከፍተኛ ደረጃ የሚከበሩ ዳኛ መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡

ክላተንበርግ የፕሪምየርሊግ ስራቸውን ለማቆም የወሰኑበት ሂደት እንዲሁም ባለፈው አመት ቶተንሀም እና ቼልሲን ሲያጫውቱ የስፐርስ ተጫዋቾችን በቀይ ማስወጣት ሲገባቸው ሆን ብለው ያለፉበት መንገድ ምክንያት ገልጸዋል፡፡

ዩናይትዶች ከስቶክ ሲቲ ጋር ተጫውተው ከሽንፈት በተረፉበት የባለፈው አመት ከሜዳቸው ውጪ ያደረጉት ጨዋታ ዋይን ሩኒ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሮ አቻ እንዲለያዩ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ሩኒ በዚህ ጨዋታ ላይ ያስቆጠረው ጎል የሰር ቦቢ ቻርልተንን የክለቡ የምንጊዜው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድ መስበር ችሏል፡፡ይህን ጨዋታ ደግሞ ያጫውቱ የነበሩት ማርክ ክላተንበርግ ነበሩ፡፡

7

ክላተንበርግ ይህን ጨዋታ ሲያጫውቱ በአንድ የጨዋታ አጋጣሚ ለዩናይትዶች የፍጹም ቅጣት ምት ሊያሰጥ የሚችል አጋጣሚ ስቶኮች በእጃቸው ቢጫወቱም አልፈውታል፡፡በዚህ ውሳኔ ደግሞ ጥሩ ስሜት ያልተሰማቸው የቡድኑ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ክፉኛ ተበሳጭተው ታይተዋል፡፡ጆሴ ንዴታቸውን ከጨዋታው በኋላ ወደ ዳኞች መልበሻ ቤት አቅንተው ማርክ ክላተንበርግ ላይ አንቧርቀዋል፡፡

ይህ የጆሴ የሰላ ትችት ክላተንበርግን የዳኝነት ስራቸው ላይ መለስ ብለው እንዲያጤኑት ያስገደደ ነበር፡፡በእለቱ ወደ ቤታቸው ለመመለስ 250 ኪሜ በመኪና መጓዝ ይጠበቅባቸው የነበሩት ክላተንበርግ በጉዟቸው ላይ ውኔያቸውን ያሰላስሉ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡የወሰንኩት ውሳኔ ልክ ነበረ? ወይስ አልነበረም..?

“ሩኒ የሰር ቦቢ ቻርልተንን ሪከርድ በሰበረበት እለት ጨዋታውን የመራሁት እኔ ነበርኩ፡፡ከጨዋታው በኋላም ሞሪንሆ ወደ መልበሻ ቤቴ መጥቶ ባልሰጠኋቸው የፍጹም ቅጣት ምት ላይ ደስተኛ አለመሆናቸውን ነገረኝ፡፡

“የስቶክ ሜዳ ሁልጊዜ ቀዝቃዛ እና አስቸጋሪ ነው፡፡ማንችስተር ዩናይትድን መዳኘትም ቀላል አይደለም፡፡ጨዋታው ካለቀ በኋላ ጥሩ እንደዳኘው ተሰምቶኝ ነበር፣ ነገርግን ሞሪንሆ ወደ መልበሻ ቤት መጥቶ ከተቸኝ በኋላ ልክ አልሰራሁም እንዴ? በማለት እራሴን መጠየቅ ጀመርኩ፡፡

“250 ኪሜ መኪና እየነዳው ወደ ቤቴ ስሄድ እራሴን ተሳስቼ ይሆን?.. እያልኩ እጠይቅ ነበር፣ባለቤቴም ባህሪዬ መለወጡን ተረድታለች፡፡በመቀጠልም ስለ ራሴ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ከአሁን በኋላ በዚህ ስራ ላይ እራሴን ለማግኘት እፈልጋለው? በእውነት ከአሁን በኋላ መዳኘት እፈልጋለው?..እያልኩኝ እጠይቃለሁ፡፡በስራው እንዳሰብኩት ብዙም ደስታ እየተሰማኝ ስላልነበረ ከስራው ለመውጣት ወሰንኩኝ፡፡ከሳውዲአረቢያ ደግሞ የስራ እድል ጥሪ ሲገጥመኝ ደግሜ ማሰብ አላስፈለገኝም፡፡ውሳኔው ቀላል ነበረ፡፡”ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

5

የቀድሞ ዳኛ አምና ቼልሲ እና ቶተንሀም ለዋንጫ ሲያደርጉት የነበረውን ፉክክር አስታውሰው እርስበርስ ጨዋታቸውን በመሩበት ወቅት የቶተንሀም ተጫዋቾች በሰሩት ጥፋት በቀይ ከሜዳ መውጣት ይገባቸው የነበረ ቢሆንም ሆን ብለው በሜዳ እንዲቆዩ ማድረጋቸውን በመናገር አወዛጋቢ አስተያት ሰጥተዋል፡፡

ስለ ጨዋታው ያስታወሱት ክላተንበርግ “ጨዋታው ትያትር ነበር፡፡እኔ የራሴ የጨዋታ እቅድ ነበረኝ፡፡ቶተንሀሞች ዋንጫ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ ምክንያታቸው እኔ መሆን እንደሌለብኝ አውቃለሁ፡፡ሶስት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ የሚያስወጣ ጥፋቶችን ሰርተው ነበር ነገርግን ግን እራሳቸውን እንዲያርሙ ፈቅጄላቸዋለው፡፡ሶስቱን ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ባስወጣቸው ኖሮ በቀጣዩ ቀን ሚዲያው እና ሰዎች በሙሉ ክላተንበርግ ቶተንሀምን ዋንጫ አሳጣ ይሉኝ ነበር፡፡”በማለት ምክንያት እንዳይሆኑ ተጫዋቾቹን በቀይ ካርድ ከማባረር እንደተቆጠቡ ተናግረዋል፡፡

ስፐርሶች ማሸነፍ ያስፈልጋቸው በነበረው ጨዋታ ላይ ክላተንበርግ ለስምንት የስፐርስ ተጫዋቾችን ቢጫ ካርድ የሰጡ ሲሆን ቼልሲዎችም ዘግይተው አቻ በመሆን የቶተንህምን የዋንጫ ተስፋ ላይ መቋጫውን እንዳበጁላቸው ይታወሳል፡፡

Advertisements