የረቡዕ ምሽት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ዳሰሳ

ዛሬ ምሽት የሚደረጉ ቀሪ የሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታዎች ማክሰኞ ምሽት ቀጣዩን 16 ክለቦች ተሳታፊነታቸውን ካረጋገጡ ገሚሱ ክለቦች በተጨማሪ ዛሬ የሚያረጋግጡ ክለቦች እንዲሁም በተጨማሪ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ያልቻሉ ነገር ግን በሶስተኛ ደረጃ የሚያጠናቅቁ 32 ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑበትን የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ውድድርን በጊዜ የሚቀላቀሉባቸውት ይሆናሉ። ተከታዩ ፅሁፍም ዛሬ ምሽት በተመሳሳይ ምሽት 4፡45 ከሚደረጉ ስምንት ጨዋታዎች መካከል ለማለፍ የሚደረግ ትንቅንቅ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠበቁ አበይት ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ያስቃኝዎታል።

ሊቨርፑል ከስፓርታክ ሞስኮ (4፡45′)

​የዚህ ምድብ ጨዋታ ከሌሎቹ ምድብ ጨዋታዎች በእጅጉ የተወሳሰበ ነው። ወደቀጣዩ ዙር አለማለፉ እርግጥ ከሆነውና  በመጨረሻ ላይ ከሚገኘው ማሪቦር ውጪ እንደቅደም ተከተላቻው ከአንድ እስከሶስት ደረጃ ላይ የሚገኙት ሊቨርፑል፣ ሲቪያና ስፓርታክ ሞስኮ ወደቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድል አላቸው። በተለይ ግን ሊቨርፑል እና የስፓርታክ ሞስኮ ሁለቱም የማለፍ ዕድል ያላቸው በመሆኑ በምድቡ ከሚደረጉ ጨዋታዎች ሁሉ ይህን ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደርገዋል። 

የእንግሊዙ ክለብ በቀዳሚነት ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ማሸነፍ ወይም ደግሞ ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ በቂው ነው። በአንፃሩ የሞስኮው ክለብ ይህን ጨዋታ መርታት የግድ ይለዋል።

ሊቨርፑል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሳፓርታክ ሞስኮ በሶስት ነጥብ፣ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሲቪያ ጋር ዳግሞ በሁለት ነጥቦች ብቻ በልጦ የተቀመጠ በመሆኑ ምንም እንኳ የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም ሊቨርፑል ወደሶስተኛ ደረጃ ዝቅ ሊል የሚችልበት አጋጣሚ አለ። ነገር ግን ስፓርታክ ይህን ለማድረግ ሊቨርፑልን ከማሸነፍም ባሻገር በመካከላቸው ያለውን የሰባት ግቦች ልዩነት ማጣፋት ይጠበቅበታል። ነገር ግን ስፓርታክ ጨዋታን ቢያሸንፍ እና ሲቪያ በማሪቦር ቢረታ ለሁለቱ ተጋጣሚዎ ሊቨርፑልና ስፓርታክ ተያይዞ ማለፍ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል። 

በአንፃሩ ስፓርታክ በሊቨርፑል ቢሸነፍ፣ ሲቪያ በማሪቦር ቢሸነፍም እንኳ በሁለተኝነት የማለፍ ዕድል ይኖረዋል።

ሌሎች ተጠባቂ ጭዋታዎች

ሁለቱም ክለቦች የማለፍ ዕድልን ይዘው ከሚያደረጉት ፍልሚያ አንፃር ከሊቨርፑልና ስፖርታክ ሞስኮ ጨዋታ ውጪ ዛሬ ምሽት በሁለት ክለቦች የማለፍ ዕድል ላይ የተመሰረተ ትንቅንቅ ያለው ጨዋታ የለም። ይሁን እንጂ ከአንድ ወገን የማለፍ ተስፋ ይዘው የሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ግን አሉ። 

በምድብ ጂ ላይ የሚገኙት ፖርቶ እና አርቢ ሌፕዚግ በግብ ተባላልጠው እኩል ሰባት ነጥቦችን ይዘው ተቀምጠዋል። ነገር ግን ሁለቱም ማለፉን ያረጋጠ እና መወደቁ እርግጥ የሆነ ክለብ የሚገጥሙ ይሆናል። የግብ ልዩነትን ከግምት ውስጥ ካስገባን ግን አርቢ ሌፕዚግ በአንደኝነት ማልፉን ባረጋገጠው ቤሽኪታሽ የሚሸነፍ ከሆነ የግብ ብዛት ብልጫ ያለው ፖርቶ ቀጥታ የማለፍ ዕድል ያገኛል። ነገር ግን ፖርቶ መውደቁን ካረጋገጠው ሞናኮ ጋር በሚያደረገው ጨዋታ አሸንፎ አርቢ ሌፕዚግ የሚሸነፍ ከሆነ ምድቡን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ይችላል። ሁለቱም ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን የሚያሸንፉ ከሆነ ግን ወደቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድላቸውን የሚወስነው በመጨረሻ ሚኖራቸው የግብ ልዩነት ብቻ ይሆናል።

ምድብ ኤፍ ላይም የቀድመው ምድብ አይነት በከፊል ተመሳይ ነገር እናገኛለን። ዘጠኝ ነጥብ ያለው ሻካታር በቀዳሚናት ማለፉን ካረጋገጠው እና የፊታችን እሁድ ትልቅ የከተማ ደርቢ ያለበትን ማንችስተር ሲቲን ይገጥማል። ይሁን እንጂ ሻካታር ወደቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሎቹ ሰፊ ናቸው። ይኸውም ጨዋታውን ማሽነፍ፣ በአቻ ውጤት ማጠናቀቀና ከእሱ በሶስት ነጥቦች አንሶ የሚጋኘው ናፖሊ በፌይኑርድ እንዲሸነፍለት ተስፋ ማድረግ ነው። 

በአንፃሩ ወደቀጣዩ ዙር እንደማያልፍ አስቀድሞ ያወቀውን ፌይኖርድን የሚገጥመው ናፖሊ የማለፍ ዕድል በእጅጉ ጠባብ ነው። ይኸውም ሻካታር በሲቲ እንዲሸነፍለት እና ተጋጣሚውን ፌይኑርድን በሰፋ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ብቻ ነው።

የምድቡ ቀዳሚ ሆኖ ለመጨረስ ከሚደረግ ፍልሚያ ውጪ ያን ያህልም የምለፍ ትንቅንቅ የሌለበት ጨዋታዎች ያለበት ምድብ ኤች ነው። በ13 ነጥቦች ምድቡን የሚመራው ቶተንሃምና በሶስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ የሚከተለው ሪያል ማድሪድ ወደቀጣዩ ዙር ማለፋቸው እርግጥ ቢሆንም የምድቡ ቀዳሚ ለመሆን በየፊናቸው ማለፍ ያልቻሉትን ዶርትሙንድና አፖል ኒኮስያን ይገጥማሉ። ይሁን እንጂ ምንም እንኳ የአንድ ግብ ልዩነት ብልጫ ቢወሰድበትም ቶተንሃም ጨዋታውን ማሸነፍ ሳይጠበቅበት ከአፓል ጋር በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ወይም የሪያል ማድሪድ ሽንፈት ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ያስችለዋል። ነገር ግን ቶተንሃም በአፖል ሽንፈት የሚፈገጥመው ከሆነና ሪያል ማድሪድ ዶርትሙንድን በማንኛውም የግብ ልዩነት የሚያሸንፍ ከሆነ የለንደኑ ክለብ የምድቡን ቀዳሚነት ለማደሪዱ ክለብ አሳልፎ የሚሰጥ ይሆናል።

የጨዋታ መርሃ ግብር – ህዳር 27

ረቡዕ ቶተንሃም 4 : 45 አፖል
ረቡዕ ሪያል ማድሪድ 4 : 45 ዶርትሙንድ
ረቡዕ ፖርቶ 4 : 45 ሞናኮ
ረቡዕ አርቢ ሌፕዚግ 4 : 45 ቤሽኪታሽ
ረቡዕ ሻካታር 4 : 45 ማን ሲቲ
ረቡዕ ፌይኑርድ 4 : 45 ናፖሊ
ረቡዕ ሊቨርፑል 4 : 45 ስፓርታክ
ረቡዕ ማሪቦር 4 : 45 ሲቪያ

ምድብ ኤ

# ክለብ ነጥብ
1 15
2 12
3 9
4 0

ምድብ ቢ

# ክለብ ነጥብ
1 15
2 15
3 3
4 3

ምድብ ሲ

# ክለብ ነጥብ
1 Previous rank: 2 11
2 Previous rank: 1 11
3 7
4 2

ምድብ ዲ

# ክለብ ነጥብ
1 14
2 11
3 7
4 1

ምድብ ዲ

# ክለብ ነጥብ
1 9
2 8
3 6
4 2

ምድብ ኤፍ

# ክለብ ነጥብ
1 15
2 9
3 6
4 0

ምድብ ጂ

# ክለብ ነጥብ
1 11
2 7
3 7
4 2

ምድብ ኤች

# ክለብ ነጥብ
1 13
2 10
3 2
4 2
Advertisements