የኢትዮጵያ ቡናን አታለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው የተነገራላቸው ኮስታዲን ፓፒች ጉዳይ

Image result for KOSTADIN PAPIC

የድራጋን ፓፓዲች የጤና እክል ተከትሎ ቡድኔን ያሰለጥኑልኛል በማለት ኢትዮጵያ ቡና ኮስታዲን ፓፒችን ቢቀጥርም አሰልጣኙ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ክለቡን ለቀው መሄዳቸው ተሰምቷል፡፡

ከዚህ ቀደም በምስራቅ ቸፍሪካ ሀያል ክለብ በሆነው ያንጋ አፍሪካ ጭምር እንደሰሩ የተነገረላቸው ኮስታዲን ፓፒች ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ወላጅ አባቴ ታሞብኛል ወደ ሀገሬ ሰርቢያ ላቀና ነው ማለታቸውን ተክትሎ ክለቡ ፍቃድ የሰጣቸው ቢሆንም

ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ግን ሰርቢያ ሳይሆን መገኛቸውን ደቡብ አፍሪካ በማድረግ ለቀድሞ ክለባቸው ሮያል ኤግልስ ፊርማ ማኖራቸው ተሰምቷል፡፡ ከቡናማዎቹ ጋር በውድድር ዘመኑ 2 ጨዋታዎችን ብቻ ያደረጉት ኮስታዲን ፓፒች በሁለቱም  ጨዋታ ድል ያደረጉ ሲሆን ከድላቸው  በኋላም ለኢትዮጵያ ቡና ባለስልጣናት የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄን አቅርበው እንደበር እና ክለቡም አጥጋቢ የሆነ ምላሽ እንዳልሰጣቸው የተነገረ ሲሆን ግለሰቡም በዚህ ተከፍተው ክለቡን በማታለል ወደ  ሮያል ኤግልስ አምርተዋል፡፡

ልማደኛው አሰልጣኝ ከዚህ ቀደምም በሌሎች ክለቦች በተመሳሳይ መልኩ የውል ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ ታመምኩ እና መሰል ምክንያቶችን በማቅረብ ቆይታቸውን እንደሚያቋጩ የታሪክ ድርሳናቸው ያሳያል፡፡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለቀጣዪቹ 2 አመታት ለመቆየት ውል የነበራቸው ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ጉዳይ አስመልክቶም ክለቡ ዛሬ ረፋድ ይፋ እንዳደረገውም አሰልጣኙ ለማሰልጠን ተስማሙ ለተባለበት የደቡብ አፍሪካው ሮያል ኤግልስ አሰልጣኙ ውል እንዳላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ መጻፉን እና ከቀጣሪ ክለቡም ምላሽ እየጠበቀ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡

Advertisements