ፖግባ ከሲቲ ጋር በሚደረገው ጨዋታ በቡድን አጋሮቹ ላይ “መቶ በመቶ” እምነት እንዳለው ገለፀ

ፖል ፖግባ ማንችስተር ዩናይትድ በእሁዱ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ አዲስ የፕሪሚየር ሊግ ሪከርድ የማስመዝገብ ተስፋቸውን እንደሚገታ በራስ መተማመን እንዳለው ገልፅዋል። 

እሁድ በሊቨርፑልና በኤቨርተን መካከል የሚደረገውን የደርቢ ጨዋታ ተከትሎ ዩናይትድ በኦልትራፎርድ 14ኛ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድል በማድረግ አዲስ ክብረወስን ማስመዝገብ የሚችለውን የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ይገጥማል።

ፖግባ ባለፈው ቅዳሜ ከአርሰናል ጋር ባደረጉት ጨዋታ በተመለከተው ቀይ ካርድ ምክኒያት እና ማንችስተር ዩናይትድም ለሶስት ጨዋታ ቅጣቱ ይግባኝ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በዚህ የደርቢ ፍልሚያ ላይ አይሰለፍም። 

አማካኙም በእሁዱ ጨዋታ ላይ ባይካተትም የቡድን አጋሮቹ ከሊጉ መሪ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ሶስት ነጥቦችን እንዲያገኙ ለቡድን አጋሮቹ ብርታት የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ተናግሯል። 

“በቡድኑ ላይ መቶ በመቶ የተሟላ እምነት አለኝ።” ሲል ፖግባ ተናግሮ “በጨዋታው ላይ ባልሰፍም። ጉልበት ለመሆን ግን አብሬያቸው እሆናለሁ። በስታዲየሙም ትልቅ ድባብ ይኖራል። ጨዋታው ትልቅ ቡድን እና ትልቅ ተጫዋቾች ያሉት ትልቅ ጨዋታ ነው።

“ይህ መጫወት የምትፈልግበት ጨዋታ ነው። ያለመታደል ሆኖ በዚህ ጨዋታ ላይ አልጫወትም። ነገር ግን ለቡድኑ አእምሯዊ ጥንካሬ እገዛ ለማድረግ በዚያ እገኛለሁ።

“ያለጥርጥርም ከሲቲ ጋር የምናደርገው ጨዋታ ነጥብ ማግኘትና ማሸነፍ የምንፈልገበት ጊዜ ነው። ወሳኝ ወቅትና ወሳኝ ጨዋታ ነው። ስለዚህ በጣም ማዘኔን መናገር እወዳለሁ።” በማለት ገልፅዋል።

ፖግባ ማንችስተር ዩናይትድ ማክሰኞ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ ሲኤስኬ ሞስኮን 2ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ 90 ደቂቃዎችን መጫወት የቻለ ሲሆን፣ በለፉት 12 አጠቃላይ ውድድሮች ላይ ሁለት ግቦችን ብቻ መረብ ላይ ያሳረፈው ሮሜሉ ሉካኩ ላስቆጠራት ግብ አመቻችቶ ማቀበልም ችሏል። 

Advertisements