በቻምፒየንስ ሊጉ እነማን ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ?የጥሎ ማለፉ ተጋጣሚዎችስ መቼ ይታወቃሉ?

የዘንድሮ የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው ወደ ቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ያለፉ 16 ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል።በቀጣይ የጥሎማለፍ ጨዋታም እነማን ሊያገናኝ ይችላል የሚለውም ከወዲሁ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።ለመሆኑ የእጣ ድልድሉ መቼ ይወጣል?16 ቱ አላፊ ቡድኖችስ እነማን ናቸው?

32 ቡድኖች በስምንት ምድብ ተከፍለው ሲያደርጉት የነበረው ጨዋታዎች ተጠናቀው ግማሾቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።የምድባቸው ሶስተኛ ሆነው ያጠናቀቁ ስምንት ቡድኖች ደግሞ ወደ ዩሮፓ ሊግ ተቀላቅለዋል።

ዘንድሮ ለየት የሚያደርገው ወደ ቀጣዩ ዙር  ከምድባቸው ሁለተኛ ሆነው ያለፉት ቡድኖች ጭምር ጠንካራ በመሆናቸው በቀጣይ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከወዲሁ ታላላቅ ፍልሚያዎች እንደሚደረጉ ይጠበቃል።

ለምሳሌ ያህል የእንግሊዙ ቼልሲ ማክሰኞ ምሽት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር 1ለ1 በመለያየቱ የምድቡ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።ይህ ደግሞ በቀጣይ ከባርሴሎና፣ፒ ኤስ ጂ ወይንም ከቤሲክታሽ ጋር ይገናኛል።

ቼልሲ ከቤኪስታሽ ውጪ ካሉት ቡድኖች ጋር ከተገናኘ በጥሎማለፉ ከሚጠበቁ አንዱ ታላቅ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ማን ዩናይትድም ቢሆን የአምና የፍጻሜ ተፋላሚዎች የነበሩት ማድሪድ ወይንም ጁቬንቱስን የማግኘት እድል ይኖረዋል።ዩይትዶች ሌሎች ሊያገኟቸው የሚችሏቸው ቡድኖች ውስጥ ባየርሙኒክ፣ሲቪላ፣ሻካታር ዶኔስክ እና ፖርቶ ይጠቀሳሉ።

የሌሎች ቡድኖችም እንዲሁ በቀጣይ ሊያገኟቸው የሚችሏቸው ቡድኖች ሲታሰብ በቀጣይ ቢያንስ ሶስት እጅግ አጓጊ የሆኑ ጨዋታዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።

ሌላው በዘንድሮ ውድድር ለየት የሚያደርገው ወደ ዩሮፓሊግ የወረዱ ቡድኖች ጠንካራ መሆን ነው።ስምንት ቡድኖች ከምድባቸው ሶስተኛ ሆነው በማጠናቀቃቸው ወደ ዩሮፓ ሊግ ተቀላቅለዋል።

ከነዚህም ውስጥ ባለፉት ቅርብ አመታት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ለፍጻሜ ደርሰው የነበሩት አትሌቲኮ ማድሪድ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ይጠቀሳሉ።

ናፖሊ፣ስፓርቲንግሊዝበን፣ሌፕዚንግ፣ስፓርታ ሞስኮ ፣ሴልቲክ እና ሲኤስ ካ ሞስኮ ደግሞ ሌሎቹ ወደ ዩሮፓሊግ የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው።

በቻምፒየንስ ሊጉ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ቡድኖች

ምድብ አንደኛ ሁለተኛ ቀጣይ ተጋጣሚዎች
1 ማን ዩናይትድ ባዜል ?
2 ፔዤ ሙኒክ  ?
3 ሮማ ቼልሲ  ?
4 ባርሴሎና ጁቬንቱስ  ?
5 ሊቨርፑል ሲቪላ
6 ማን ሲቲ ሻካታር ዶ  ?
7 ቤሲክታሽ ፖርቶ  ?
8 ቶተንሀም ማድሪድ ?

በቻምፒየንስ ሊጉ ወደ ቀጣዩ 16 የተቀላቀሉ ቡድኖች በጥሎ ማለፍ የሚገጥሟቸውን ቡድኖች በስዊዘርላንድ ኒዮን  የፊታችን ሰኞ  በፈረንጆቹ ታህሳስ 11 ላይ በሚወጣው እጣ ማውጣት ስነ ስርአት የሚታወቅ ይሆናል፡፡

እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአንድ ምድብ ላይ የነበሩ ቡድኖች እና የአንድ ሀገር ቡድኖች እርስ በርስ የመገናኘት እድል አያገኙም፡፡ምድባቸውን በአንደኝነት ያጠናቀቁ ቡድኖች ደግሞ የጥሎ ማለፉን የመልስ ጨዋታ በሜዳቸው የማድረግ እድል ያገኛሉ፡፡

የመጀመሪያ ጨዋታዎችም በፈረንጆቹ የካቲት 13/14 እንዲሁም የካቲት 20/21 ሲደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ መጋቢት 6/7 እንዲሁም መጋቢት 13/14 ተደርገው ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚቀላቀሉ ቡድኖች ይለያሉ፡፡

Advertisements