ባሎንዶር / የ 2017 የባሎንዶር አሸናፊ ዛሬ ይፋ ይደረጋል

የፍራንስ ፉትቦል የ2017 የባሎንዶር አሸናፊ ለ62ኛ ጊዜ ዛሬ ይፋ ሲደረግ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወይም ሊዮ ሜሲ ሌላ ተጫዋች ጣልቃ ሳያስገቡ ለዘጠነኛ ተከታታይ አመት በድጋሚ ከሁለት አንዳቸው አሸናፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

ሁለቱ ኮከቦች ብራዚላዊው ካካ 2007 ላይ አሸናፊ ከሆነ በኋላ ላለፉት ረጅም አመታት እየተፈራረቁ የባሎንዶር አሸናፊ መሆን ችለዋል።

ሊዮ ሜሲ አምስት ጊዜ በማሸነፍ ብዙ ጊዜ ባሎንዶርን በማሸነፍ ቅድሚያውን የያዘ ሲሆን ክርስቲያኖ ሮናልዶ በበኩሉ እስከ 2016 ድረስ አራት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።ዘንድሮስ?

ክርስቲያኖ ሮናልዶ  የላሊጋ እና የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫ ከማድሪድ ጋር በማንሳት ድንቅ አመትን በማሳለፉ የ2017 ባሎንዶር ለአምስተኛ ጊዜ እንደሚያሸንፍ ቅድሚያውን ይዟል።

ሮናልዶ ለአምስተኛ ጊዜ አሸናፊ ለመሆን ቅድሚያውን ይዟል

በቻምፕየንስ ሊጉ ጁቬንቱስን በማሸነፍ ማድሪድ ለሁለተኛ ተከታታይ አመት ባለ ትልቁን ጆሮ እንዲያገኝ አስችሏል።

ፖርቹጋላዊው ኮከብ አሸናፊ ከሆነ ከሌላው ኮከብ ሊዮ ሜሲ እኩል ለአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊነት ክብር ይቀዳጃል።

ሜሲ እና ኔይማር ሮናልዶን ተከትለው አሸናፊ የመሆን እድል ያላቸው ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

አሸናፊው መቼ ይፋ ይሆናል?

የ2017 የባሎንዶር አሸናፊ ዛሬ [ሀሙስ] በፓሪስ ኤፈልታወር ጎን ሽልማቱን ይቀበላል።

የፕሮግራሙ መሪ

የቀድሞ የቶተንሀም እና የኒውካስትል ተጫዋች የነበረው ፈረንሳዊው ዴቪድ ጅኖላ ፕሮግራሙን ይመራዋል።

አሸናፊው ስንት ሰአት ላይ ይታወቃል?

ከምሽቱ 3:00

አሸናፊው እንዴት ይለያል?

በፍራንስ ፉትቦል መፅሄት አማካኝነት አለም ላይ ያሉ 173 ጋዜጠኞች በምርጫው ላይ ተሳታፊ አድርገዋል።

ሮናልዶ ወይስ ሜሲ?

የ2017 የባሎንዶር እጩዎች

ኔይማር – ፔዤ

ንጎሎ ካንቴ – ቼልሲ

ሉካ ሞድሪች – ማድሪድ

ፓውሎ ዲባላ – ጁቬንቱስ

ማርሴሎ – ማድሪድ

ኤዲን ዜኮ – ሮማ

ሀሪ ኬን – ቶተንሀም

ዴቪድ ዴሂያ – ማን ዩናይትድ

ሮበርት ሌዋንዶውስኪ – ሙኒክ

ኬቪን ደብሮይን – ማን ሲቲ

ካሪም ቤንዜማ – ማድሪድ

ፒየር ኤምሪክ አውበሚያንግ – ዶርትሙንድ

ኤዲሰን ካቫኒ – ፔዤ

ፍሊፔ ኮቲንሆ – ሊቨርፑል

ልዊስ ስዋሬዝ – ባርሴሎና

ጃን ኦብላክ – አት ማድሪድ

ሰርጂዮ ራሞስ – ማድሪድ

ድረስ መርተንስ – ናፖሊ

ራዳሚል ፋልካኦ – ሞናኮ

ሳዲዮ ማኔ – ሊቨርፑል

ጂጂ ቡፎን – ጁቬንቱስ

አንቶይን ግሪዝማን – አት ማድሪድ

ቶኒ ክሩስ – ማድሪድ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ – ማድሪድ

ኤደን ሀዛርድ – ቼልሲ

ሊዮናርዶ ቦኑቺ – ሚላን

ኢስኮ – ማድሪድ 

ሊዮ ሜሲ – ባርሴሎና

ማትስ ሁመልስ – ሙኒክ

ኪልያን ምባፔ – ፔዤ

የ2016 አሸናፊ ማን ነበር?

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእለተ ሰኞ የ2016 የባሎንዶር አሸናፊ በመሆን ለአራተኛ ጊዜ ባለ ክብር መሆኑ ይታወቃል።ተጫዋቹ ለ 11ኛ ጊዜ የቻምፕየንስ ሊጉን ዋንጫ ከማድሪድ ጋር እንዲሁም የአውሮፓ ዋንጫ ከፖርቹጋል ጋር ማንሳቱ አሸናፊ እንዲሆን እንደረዳው ይታወሳል።

ውድ የድረገፃችን አንባቢዎች እርሶስ ማን አሸናፊ ይሆናል ይላሉ? ሀሳቦትን በኮሜንት መስጫ ላይ ያካፍሉን።

Advertisements