ዲየጎ ፔሮቲ ከሮማ ጋር ያለውን ኮንታርት አደሰ

ዲየጎ ፔሮቲ ሃሙስ ጠዋት ከሮማ ጋር ያለውን ኮንትራት ማደሱን መግለፁን ተከትሎ የክንፍ ተጫዋቹ አዲስ ኮንታራት መፈረሙን ክለቡ በይፋ ገልፅዋል።

ተጫዋቹ አስቀድሞ በማህበራዊ ገፁ ከክለቡ ጋር የነበረውን ኮንትራት እ.ኤ.አ. እስከ2021 ድረስ ማራዘሙን ገልፆ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ጂያሎሮሲዎቹ በይፋዊ ድረገፃቸው ላይ ባወጡት መግለጫ ለዜናው ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

“ኤኤስ ሮማ የፊት ተጫዋቹ ዲየጎ ፔሮቲ ከክለቡ ጋር አዲስ ኮንትራት መፈራረሙን ሲገልፅ በደስታ ነው።” ሲል የክለቡ መግለጫ አስነብቧል።

“የ29 ዓመቱ የአርጄንቲና ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ከክለቡ ጋር እስከ ሰኔ 2021 ድረስ ለመቆየት ውሳኔ ላይ በመድረስ ከጂያሎሮሲዎቹ ጋር የሁለት ዓመታት የውል ማራዘሚያ ፊርማ ፈርሟል።

“ፔሮቲ ሮማን በ2016 ተቀላቅሎ በሁሉም ውድድሮች ላይ 78 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫዋቷል፤ 17 ግቦችንም አስቆጥሯል።” ሲል የጣሊያኑ ክለብ መግለጫ ገልፃዋል።

Advertisements