“ማንችስተር ሲቲን የማቆም አቅም አለን” ዲቪድ ደሂያ

629690-david-de-gea-manchester-united-vs-arsenal

የፊታችን እሁድ በታላቁ የማንችስተር ደርቢ ሁለቱ የእንግሊዝ ሀያላን ክለቦች በሊጉ 16ኛ ሳምንት ጨዋታ በኦልድ ትራፎድ ይገናኛሉ፡፡ በዚህ ተጠባቂ ጨዋታም ከወዲሁ በርካቶች የቅድመ ማሸነፍ ግምቱን ለማንችስተር ሲቲ ቢሰጡም የቀያዮቹ ሰይጣኖች የግብ ዘብ የሆነው ዲቪድ ደጊያ ግን ዩናይትድ ሲቲን የማቆም አቅም አለው ሲል ከጨዋታው በፊት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ማንችስተር ዩናይትድ አርሰናልን 3-1 በረታበት ጨዋታ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት 14 ያለቀላቸውን የግብ ሙከራዎች በማምከን በሊጉ በውድድር ዘመኑ አዲስ ታሪክ የቻለው ስፔናዊው ኮከብ ዴቪድ ደሂያ ከስካይ ስፖርቱ ተንታኝ ቴሪ ዳንኤል ሄነሪ ጋር ባደረገው ቆይታ “እኛ በሜዳችን እና በደጋፊያችን ፊት ነው ይህንን ጨዋታ የምናደርገው ይህ ደግሞ በራስ መተማመናችንን ከማሳደጉም በላይ ጨዋታውን በድል እንድንወጣ ያስችለናል፡፡”

“ክለባችን በአሁኑ ሰዓት በጥሩ መንፈስ ላይ ይገኛል፡፡ ከሜዳችን ውጪ ያደረግናቸው ሁለት ተከታታይ ጠንካራ ጨዋታዎች አሸንፈን ተመልስናል፡፡ አሁንም የምናደርገውን ጨዋታ ሁላችንም ማሸነፍ እንፈልጋለን፡፡  ሲል ማንችተር ዩናይትድ ጨዋታውን የማሸነፍ አቅም እንዳለው አብራርቷል፡፡”

ማንችስተር ሲቲ የፊታችን እሁድ የሚደረገውን የደርቢ ጨዋታ ማሸነፍ የሚችል ከሆነ በሊጉ ታሪክ በአርሰናል ተይዞ የነበረውን 14 ተከታታይ የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች የማሸነፍ ክብረወሰን የሚጋራ ሲሆን ማንችስተር ዩናይዶች ደግሞ በሜዳቸው ያደረጉትን 40 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ክብረ ወሰን የሚያስቀጥሉ ይሆናል ፡፡

Advertisements