አርሰናል በዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ  ጨዋታ እነማን ያገኛል?ተጋጣሚውንስ መቼ ያውቃል?

ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊጉ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የዩሮፓሊግ ውድድር በ 12 ምድቦች 48 ቡድኖች ሲያደርጉት የነበረው የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው ወደ ቀጣዩ ዙር አላፊ ቡድኖች ተለይተው ታውቋል።

24 ቡድኖች፣ከቻምፒየንስ ሊጉ ሶስተኛ ደረጃን ያገኙ ስምንት ቡድኖችን ጨምሮ በአጠቃላይ 32 ቡድኖች በጥሎ ማለፉ ጨዋታ ላይ ቀጣይ ተጋጣሚያቸውን ይጠብቃሉ።

ዘንድሮ ከሌላው አመት ለየት የሚያደርገው ከቻምፒየንስ ሊጉ ሶስተኛ ደረጃን አግኝተው ወደ ዩሮፓ ሊግ የተቀላቀሉት ቡድኖች ጠንካራ በመሆናቸው በጥሎማለፉ ጠንካራ ፉክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።

 የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ናፓሊ፣ሴልቲክ፣ስፓርቲንግ ሊዝበን፣ሲኤስካ ሞስኮ፣ስፓርታ ሞስኮ እና ራቢ ሬፕዚንግ ወደ ዩሮፓ ሊግ የተቀላቀሉ ስምንቱ ቡድኖች ናቸው።

 32 ቱ ቡድኖች የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚያቸው የፊታችን ሰኞ በስዊዘርላንድ ኒዮን በሚወጣው የእጣ ማውጣት ስነስርአት የሚያውቁ ይሆናል።

ከየምድቡ አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ 12 ቡድኖች ከቻምፒየንስ ሊጉ የተቀላቀሉ አራት የተመረጡ ቡድኖች በአጠቃላይ 16 ቡድኖች እርስበርስ የማይገናኙ ሲሆን ከምድባቸው ሁለተኛ ከወጡ እና ከቀሪዎቹ አራት ከቻምፒየንስ ሊጉ ከወረዱት ቡድኖች ጋር ከአንዳቸው በእጣ ተጋጣሚያቸውን ያውቃሉ።

ይህ ማለት አትሌቲኮ ማድሪድ፣ሲኤስካ ሞስኮ፣ሌፕዚንግ እና ስፓርቲንግ ሊዝበን ከቻምፒየንስ ሊጉ ሶሰተኛ ሆነው ቢያጠናቅቁም በዩሮፓ ሊጉ ከምድባቸው አንደኛ ከወጡት ጋር  እርስበርስ እንዳይገናኙ ተደርጓል።

በተጨማሪ የየምድባቸው አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖች ከምድባቸው ሁለተኛ ሆነው ካጠናቀቁ ቡድኖች ጋር በቀጣዩ የጥሎማለፍ ጨዋታ ላይ አይገናኙም።

በዚህ መሰረት የእንግሊዙ አርሰናል ከምድብ ስምንት አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን ከምድቡ ሁለተኛ ሆኖ ካጠናቀቀው ሬድስታር ቤልግሬድ ጋር በጥሎ ማለፍ አይገናኝም።

ስለዚህ አርሰናል ከሌሎች ምድቦች ሁለተኛ ሆነው ካጠናቀቁ እንዲሁም ከቻምፒየንስ ሊጉ ወደ ዩሮፓ ሊግ ከወረዱት ከስምንቱ ቡድኖች ውስጥ ከአራቱ [ናፖሊ፣ዶርትሙንድ፣ሴልቲክ እና ስፓርታ ሞስኮ] በአጠቃላይ ከ15 ቡድኖች አንዱ ጋር ይገናኛል።

በአጠቃላይ አርሰናል ሊያገኛቸው የሚችላቸው 15 ቡድኖች 

1) ኤኢኬ አቴንስ

2) ዶርትሙንድ

3) ሴልቲክ

4) ኤፍሲ አስታና

5) ኤፍሲ ኮፐንሀገን

6) ሉዶጎሪትስ

7) ላዛግራድ

8) ሊዮን

9) ማርሴ

10) ናፖሊ

11) ኒስ

12) ኦስቴሩስንድስ

13) ፓርቲዢያን ቤልግሬድ

14) ሪያል ሶሴዳድ

15) ስፓርታክ ሞስኮ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ደምቀው የተፃፉት ከአርሰናል ጋር የሚገናኙ ከሆነ ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

 

Advertisements