“ከ ማን ዩናይትድ ቡድን ውስጥ የማን ሲቲን ማሊያ ለመልበስ የሚችሉት አራት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው።” – አለን ሺረር


የቀድሞ የብላክበርን እና የኒውካስትል ተጫዋች የነበረው እንግሊዛዊው አለን ሺረር ከወቅቱ የማንችስተር ዩናይትድ የቡድን ስብስብ ውስጥ አራት ተጫዋቾች ብቻ የማንችስተር ሲቲን ማሊያ መልበስ የሚችሉ መሆኑን ተናገረ።

በሳምንቱ መጨረሻ ከሚጠበቁ ታላላቅ ጨዋታዎች ውስጥ ዋነኛው የሆነው መቀመጫቸውን በማንችስተር ያደረጉት ማን ዩናይትድ ከ ማን ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።

ቀዮቹ በሜዳቸው ኦልድትራፎርድ “ጩኸታሞቹ ጎረቤቶች”ከሚሏቸው እና በፕሪምየርሊጉ አናት ላይ ተንደላቀው የተቀመጡትን ማን ሲቲዎችን በማሸነፍ በመካከላቸው ያለው የስምንት ነጥብ ልቱነት ለማጥበብ እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።

ነገርግን የመሀል ሜዳ ሞተራቸው የሆነው ፖል ፓግባን በቅጣት በማጣታቸው ጠንካራውን የፔፕ ጓርዲዬላ ስብስብን እንዴት ሊቋቋሙ ይችላሉ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።

ሲቲዎች ይህን ጨዋታ ማሸነፍ የሚችሉ ከሆነ ገና የውድድሩ አጋማሽ ሳይደርስ ከተከታዬቻቸው ቡድኖች በርቀት ተቀምጠው ለዋንጫ የሚያደርጉት ሩጫ አጠናክረው ይቀጥላሉ።

ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፊት የቀድሞ ተጫዋቾች ሀሳባቸው እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አለን ሺረር እና ኢያን ራይት ይገኙበታል።

ሁለቱን ቡድኖች ያነፃፃሩት ሺረር እና ራይት አብዛኛዎቹ የማን ዩናይትድ ተጫዋቾች የሲቲን ሚሊያ ለመልበስ ብቁ አለመሆናቸው ተስማምተውበታል።

ነገርግን ሺረር ከወቅቱ የማን ዩናይትድ ተጫዋቾች ውስጥ አራት ተጫዋቾች በሲቲ መሰለፍ እንደሚችሉ ሀሳቡን ሲሰጥ ኢያን ራይት በበኩሉ ሶስት ተጫዋቾች ብቻ ምርጫው አድርጓል። 

ሺረር ፖግባን  ቤይሊ፣ቫሌንሺያ እና ዴሂያ ምርጫው ሲያደርግ ኢያን ራይት በበኩሉ ከቫሌንሺያ ይልቅ የሲቲው ካይል ዎከርን የተሻለ በመሆኑ ቫሌንሺያ ምርጫው አለመሆኑ አሳውቋል።

“ቫሌንሺያ ሲጫወት ደስ ይለኛል፣ነገርግን የሲቲው ዎከርን እወደዋለው።ስለዚህ ከዎከር ውጪ በዛ ቦታ ላይ የምመርጠው ተጫዋች አይኖርም።” ሲል ኢያን ራይት ተናግሯል።

Advertisements